አለም አቀፍ የወባ መድሃኒት አቅርቦትን ለመጨመር እየተሰራ ነው

Artemesinin Image copyright Ying Liu / Xinhua

ተመራማሪዎች የወባ በሸታ መድሃኒት ለመስራት የሚጠቅም ተክል ምርትን በመጨመር የአለም አቀፉ የወባ መድሃኒት ፍላጎትን ለማሟላት አስበዋል።

የተመራማሪዎቹ ይህ የወባ በሸታ መድሃኒት መስሪያ የሚውለውን አርሚሲያ አኑዋ የተባለ ተክል ዘረ መል በማሻሻል ምርቱን ሌሎች ፋብሪካዎች ከሚያመርቱት በ3 እጥፍ ማሳደግ መቻላቸው ተገልጿል።

የፋብሪካዎች የመድሃኒት ምርት ዘወትር የወባ መድሃኒት ፍላጎትን አያሟላም።ምክንያቱም ተክሎቹ ተፈላጊውን ንጥረ ነገር በቢቂ ሁኔታ ስለማያዘጋጁ ነው።

ከሻንግሃይ ጂያዮ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ውጤቱን ይፋ ካደረጉት መካከል አንዱ የሆነው ኬዡአን ታንግ እንደሚለው ከአለም ህዝብ ግማሽ የሚሆነው በወባ በሽታ የመጠቃት እደሉ ሰፊ ነው።

"የጀመርነው አርሚሲያን በብዛት የማምረት ስራ አለማቀፉን የወባ መድሃኒት ፍላጎት ከማሟላት አልፎ የጤና እክሎችንም ይከላላከላሉ" ይላል።

የተመራማሪዎች ቡድኑ አርሚሲኒን የተባለው ተክል ላይ ምርምር አካሂዶ የዘረ መል ማሻሻያ በማድረግ ጥራትና ምርቱን መጨመር ችለዋል።

አለም አቀፉ የጤና ድርጅት እንደሚለው የወባ በሽታ እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 ብቻ በ 91 አገራት የሚገኙ 216 ሚሊዮን ሰዎችን ያጠቃ ሲሆን በዚያው ዓመት 445,000 ሰዎችን ደግሞ ለሞት ዳርጓል።

በአሁኑ ወቅት የወባ በሸታ መድሃኒት ለማምረት ጥቅም ላይ ከሚውሉ ተክሎች መካከል፤ አርሚሲያ አኑዋ የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት ይሁንታን ያገኘ ብቸኛው ተክል መሆኑን የኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ላን ግራሃም ይናገራሉ።

ፕሮፌሰሩ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ይህ ግኝት ትልቅና የወባ በሽታን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ሚያግዝ እንደሆነ ተናግረዋል።