ላውሮ ማንችስተር አርሴናልን ይረታል ይላል

ወደ መገባደዱ የተቃረበው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በሳምንቱ መጨረሻ ብዙ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል። የትኞቹ ቡድኖች ሦስት ነጥብ ይዘው ይወጡ ይሆን? እነማንስ ተሸናፊ ይሆናሉ? የቢቢሲው ስፖርት ተንታኝ ላውሮ ግምቱን አስቀምጧል።

ሊቨርፑል ለስቶክ

2-0

ሊቨርፑሎች ስቶክን በሚያስተናግድበት የቅዳሜ ምሳ ሰዓት ጨዋታ፤ ከሮማ ጋር የነበራቸውን ድንቅ ብቃት ይደግማሉ ያለው ላውሮ ጨዋታው በሊቨርፑል 2 ለ ባዶ አሸናፊነት ይጠናቀቃል ብሏል።

በርንሌይ ከ ብራይተን ባዶ ለ ባዶ እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ከ ሌስተር ሲቲ 1 ለ 1 ይለያያሉ ሲል ግምቱን አስቀምጧል።

ኤቨርተንን የሚያስተናግዱት ሃደርስፊልዶች 1 ለ ባዶ ያሸንፋሉ ብሎ ላውሮ የገመተ ሲሆን ዌስት ብሮም ደግሞ በኒውካስል 2 ለ ባዶ ይሸነፋል።

ሳውዝሃምፕተኖች ከበርንማውዝ በሚያደርጉት ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ያሸንፋሉ ያለው ላውሮ፤ ቼልሲዎች ደግሞ ስዋንሲ ሲቲን 2 ለ ባዶ ያሸንፋሉ።

ስዋንሲ ከ ቼልሲ

2-0

ቀድመው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን መሆናቸውን ቢያረጋግጡም፤ ማንቸስተር ሲቲዎች ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩናል የሚለው ላውሮ፤ እሁድ ዌስት ሃምን ያለ ምንም ጥርጥር 2 ለ ባዶ ይረታሉ ብሏል።

ዌስትሃም ዩናይትድ ከ ማንችስተር ሲቲ

2-0

በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ አርሰናልን ያስተናግዳል። ምንም እንኳን በአውሮፓ ሊግ ጨዋታ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር አቻ ቢለያዩም፤ አርሰናሎች በጥሩ አቋም ዩናይትድን ይገጥማሉ ተብሎ ይጠበቃል። እንደ ላውሮ ግምት ከሆነ ግን ዩናይትዶች 2 ለ ባዶ ያሸንፋሉ።

ማንችስተር ዩናይትድ ከ አርሰናል

2-0

ሃሪ ኬን ከጉዳቱ በደንብ ያላገገመላቸው ቶተንሃሞች ዋትፎርድን በሚያስተናግዱበት የሰኞ ምሽት ጨዋታ 2 ለ ባዶ ያሸንፋሉ ሲል ላውሮ ግምቱን አስቀምጧል።

ቶተንሃም ከ ዋትፎርድ

2-0

ተያያዥ ርዕሶች