አንድ በሞቴ!

የጉርሻ ዝግጅት

ባሳለፈነው ቅዳሜ በጊዮን ሆቴል ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ተሰባስበው በሙዚቃ ድግስ ላይ ተጎራርሰዋል።

አዘጋጆቹ ክስተቱ ቋሚ የጉርሻ ቀን ሆኖ እንዲሰየም ይፋልጋሉ። በኢትዮጰያ የማይቋረጥ ዓመታዊ የመጎራረስ ፌስቲቫል እንዲኖር ያልማሉ። ከፍ ሲልም ጉርሻን በማይዳሰስ ቅርስነት የማስመዝገብ የረዥም ጊዜ ትልምን ሰንቀዋል።

5 ሺህ ጉርሻዎች!

በቅዳሜው ኩነት ላይ 5ሺ ሰዎችን በማሳተፍ በጊነስ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ለማስፈር ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በተለያየ ምክንያቶች ሳይሳካ ቀርቷል።

በፕሮግራሙ ላይ ወደ 1700 የሚጠጉ ሰዎች ተገኘተው እንደነበር አስተናጋጆቹ ተናግረዋል።

ከአዘጋጆቹ መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ አብረሃም "እንደ ጉርሻ ግን የሚያግባባን የለም. . . ጉርሻ እኮ አንዱ ለሌላው የማጉረስ ተግባር ብቻ አይደለም፤ በተጠቀለለው እንጀራ ውስጥ ፍቅር አለ፣ መተሳሰብ አለ፣ አክብሮት አለ።" ሲል ከዝግጅቱ በፊት ተናግሮ ነበር።

5 ሺህ ጉርሻዎች!

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ