የኬንያ ፍርድ ቤት ከፍቺ በኋላ ንብረት እኩል መካፈልን ውድቅ አደረገ

Divorce Image copyright Getty Images

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጋብቻ የተሳሰሩ ጥንዶች በጋራ የሚያፈሯቸውን ንብረቶች ሲፋቱ እኩል ተካፋይ እንዲሆኑ የቀረበለትን ጥያቄ ፍትሃዊ አይደደለም በማለት ውድቅ አደረገ።

የህግ ባለሙያ ሴቶች ፌደሬሽን በበኩላቸው የፍርድቤቱ ውሳኔ ህገ መንግስታዊ ያልሆነና ፍትሃዊ ያልሆነ ሲሉ ገልፀውታል።

"ሰዎች ወደ ጋብቻ እንዲያመሩ ሳይሆን የሚገባቸውን ይዘው እንዲወጡ የሚያበረታታ ነው" ሲሉ ዳኛ ጆን ማቲቮ ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤቱ ሴቶች በፍቺ የተለዩት የቀድሞ ባላቸው ካሳ እንዲከፍላቸው አሊያም ንብረት እንዲያካፍላቸው የጠየቁትን ቅሬታ ሰምቶ ነበር። ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ግን "ይህን ለመወሰን ስልጣን የለኝም። ይህ የቤተሰብ ጉዳይ ነው" ሲል ነበር የመለሰው።