ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ውይይት ሰረዙ

ትራምፕና ኪም ጆንግ ኡን Image copyright Getty Images

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆን ኡንግ ጋር ለማድረግ አቅደውት የነበረውን ንግግር መሰረዛቸው ተሰምቷል።

ትራምፕ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ''ጥልቅ ንዴት እና ግልፅ ጥላቻን'' ያሳያል ያሉትን የሰሜን ኮሪያ መግለጫ ምክንያት አድርገው እንደሆነ ይፋ አድርገዋል።

በዚህ ሁኔታ ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ በሲንጋፑር ሊደረግ በነበረው ጉባኤ ላይ መገኘት ''ተገቢ አይደለም'' ያሉት ትራምፕ፤ ለኪም ጆንግ ኡን በፃፉት ደብዳቤ ላይ ይሄ ነው ብለው ባልጠቀሱት ቀን ከሰሜን ኮሪያው መሪ ጋር ለመገናኘት እንደሚሹ አሳውቀዋል።