ኤርትራ ውስጥ በአጋጠመ የመኪና አደጋ 33 ሰዎች ሞቱ

ከአስመራ በስተ ሰሜናዊ ምዕራብ ሽንድዋ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተገለበጠው አውቶቡስ Image copyright ERI-TV

ትላንትና ግንቦት 20 ረፋዱ ላይ ከአስመራ ወደ ከረን በሚወስድ መንገድ በአጋጠመ የአውቶቡስ አደጋ 33 ሰዎች እንደሞቱ መንግስታዊው የዜና ማዕከል አስታወቀ።

ከአስመራ በስተ ሰሜናዊ ምዕራብ ሽንድዋ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በአጋጠመ የአውቶቡስ መገልበጥ አደጋ ሹፌሩን ጨምሮ 11 ሰዎች በጽኑ በመቁሰላቸው ለከፍተኛ ህክምና አስመራ በሚገኘው ሐሊበት ሆስፒታል እንደተወሰዱ ዜናው በተጨማሪ አረጋግጧል።

አውቶቡሱ፣ አመታዊውን የቅድስት ማርያም ክብረ-በዓልን ለማክበር የሚጓዙ 45 ሰዎች የጫነ እንደነበርና መንገዱን ስቶ 80 ሜትር ጥልቀት ያለው ገደል ውስጥ መግባቱ ተገልጧል።

አደጋው የደረሰው ከተገቢው ፍጥነት በላይ በማሽከርከር ሊሆን እንደሚችል ምርመራውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው የኤርትራ ትራፊክ ፖሊስ ጽሐፈት ቤት መግለጡን የመገናኛ ብዙሃኑ ዘገባ ያስረዳል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ