ለአንድ ወር ከአልኮል መታቀብ በጤናችን ላይ የሚኖረው አስደናቂ ውጤት

አልኮል መጠጣት አቁሚያለሁ Image copyright ISTOCK / GETTY IMAGES

በመጀመሪያው ሳምንት በጣም ከባድ ነው፤ በአስራ አምስተኛው ቀን እየቀለለ ይሄዳል፤ በሃያ ዘጠነኛው እና በሰላሳኛው ቀን የተለየ ስሜት ይሰማናል ከዚያም ሰውነታችን ምስጋና ያቀርባል።

ለአንድ ወር ያህል ከአልኮል መጠጥ መታቀብ በጤና ላይ እጅግ ጠቃሚ ውጤት እንደሚያስገኝ የሚሳይ ጥናት ይፋ ተደርጓል። ጥናቱ የመጀመሪያ እንደሆነም ተነግሮለታል።

በለንደን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተካሄደው የዚህ ጥናት ዓላማ የምግብ መዋሃድ ሂደትን (Metabolism) በተለይ ደግሞ ለካንሰር በሽታ ምክንያት የሚሆን የአመጋገብ ሥርዓትን፤ ለተወሰነ ጊዜ የአልኮል መጠጥን ከመተው ጋር በማገናኘት መዳሰስ ነው።

በጥናቱ ከአልኮል የታቀቡት ሰዎች የኮሌስትሮል መጠናቸው ፣ የሰውነት ክብደታቸው እንዲሁም የደም ዝውውራቸው ላይ አወንታዊ ውጤት ታይቷል።

ሌላኛው በቅርቡ የይፋ የሆነው የጥናቱ ግኝት እንደሚያስረዳው አልኮል መጠጣት ካንሰርን የሚያስከትሉ ሴሎችን እድገት ያፋጥናል። በዚህም አይነት ሁለት የስኳር በሽታና የጉበት በሸታን ያስከትላል።

በተመራማሪዎቹ ጉአታም መህታ፣ ስቴዋርት ማክዶናልድ እና አሌክሳንድራ ክሮንበርግ የተመራው ይህ ጥናት አልኮል ለአካል ጉዳት ብሎም ለሞት በማይዳርጉ በሽታዎች ምክንያት ሞትን በማስከተል ዋነኛ ሰበብ ይሆናል።

"ጥናቱ የአልኮል መጠጥ አልፎ አልፎ እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ የሚወስዱ 141 ሰዎች የተሳተፉበት ሲሆን፤ ሁሉም ሰዎች በአማካይ ከሚፈቀድላቸው እጥፍ በላይ የአልኮል መጠጥን ይጠቀማሉ" ሲል አንዲይ ኮግላን የተባለው ተመራማሪ ገልጿል።

Image copyright ISTOCK / GETTY IMAGES

በጥናቱ ከተካተቱት ሰዎች 94ቱ ሙሉ በሙሉ አልኮል እንዲያቆሙ ሲደረጉ ቀሪዎቹ የነበራቸውን ልምድ እንዲቀጥሉ ተደረገ።

የመጀመሪያው ቡድን ተሳታፊዎች እድሜያቸው ወደ አርባ ስድስት የሚጠጋ 43 ወንዶችና 51 ሴቶች ናቸው።

ሁለተኛው ቡድን ደግሞ 47 ተሳታፊዎች ሲኖሩት 22 ወንዶችና 25 ሴቶች የነበሩበት ሲሆን እድሜያቸው በአማካይ ወደ አርባ ዘጠኝ የሚጠጋ ነው።

ከሁሉም ተሳታፊዎች አልኮል ከማቆማቸው በፊትና ከአልኮል ከታቀቡ ከአንድ ወር በኋላ የደም ናሙና ተወሰደ።

የአልኮል መጠጥን ለወራት ያሀል ከመውሰድ የታቀቡት ተሳታፊዎች በሰውነታቸው ላይ የኢንሱሊን አመራረት ላይ አወንታዊ የሆነ ለውጥ ለመታየት ችሏል። ይህም በሰውነታቸው ያለውን የስኳር መጠን ጤናማ እንዲሆን አድርጎታል።

"ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ከተፈለገው በላይ አልኮል መጠጣት ለአይነት ሁለት የስኳር በሸታ የመጋለጥ እድልን ያሰፋዋል" ሲሉ ከአጥኝዎቹ አንዷ የሆኑት መህታ ተናግረዋል።

ምንም እንኳን የአልኮል መጠጥ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ጋር መያያዙ አዲስ ነገር ባይሆንም ከአልኮል መታቀባቸው ተሳታፊዎቹ ክብደታቸውን ለመቆጣጠር ረድቷቸዋል።

አልኮል አዘውትሮ የመጠጣት ችግር ያለባቸው ሰዎችም የጤና ባለሙያ እንዲያማክሩና የአልኮል መጠጥ ፍጆታቸውን እንዲቀንሱ ጥናቱ መክሯል።

ተያያዥ ርዕሶች