በኬንያ ናይሮቢ 15 ሰዎች በእሳት ቃጠሎ ሕይወታቸውን አጡ

ጊኮምባ ገበያ ስፍራ Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ጊኮምባ በኬኒያ ታዋቂ ከሆኑ ገበያዎች መካከል አንዱ ነው

በኬኒያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የገበያ ሥፍራ በተነሳ እሳት 15 ሰዎች ሞቱ። እሳቱ እኩለ ሌሊት ላይ የጀመረ ሲሆን 50 ሰዎች በነበልባሉ ጉደት ደረሶባቸዋል።

ጊኮምባ በከተማው ካሉ ትልልቅ የገበያ ሥፍራዎች መካከል አንዱ ሲሆን በተደጋጋሚ ቃጠሎ ደርሶበታል።

የትናንት ለሊቱ ቃጠሎ መነሻ ምክንያት ምን እንደሆነ እስካሁን ድረስ አልታወቀም።

ታላቁ አንዋር መስጊድ ከእሳት ተረፈ

የሴይን ጆን የአምቡላንስ አገልግሎት እሳቱ ለሊት 8 ሰዓት ተኩል ላይ እንደጀመረ ገልጾ በ90 ደቂቃዎች ውስጥ ከሱቆች ወደ አፓርትመንቶች መዛመቱን ተናግረዋል።

አንዳንድ ሰዎች ንብረታቸውን ከእሳት ለማትረፍ ሲሯሯጡ የተቃጠሉ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ጭሱን በመተንፈስ እንደተጎዱ ተገልጿል።

የሆስፒታል ምንጮች ከሟቾቹ መካከል 4 ሕጻናት እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች ሕክምና እያገኙ ነው።

ገበያው ልባሽ ጨርቆች፣ ጫማዎች፣ አትክልትና ጣውላ የሚሸጥበት ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ