በናይጄሪያ የነዳጅ ጫኝ መኪና በእሳት ተያይዞ የዘጠኝ ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ

በናይጄሪያ ሌጎስ እግረኛ ከእሳቱ ለመሸሽ ሲሮጥ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ በናይጄሪያ ሌጎስ ነዳጅ የጫነ መኪና ፍሬኑ እምቢ ካለው በኋላ ተገልብጦ በእሳት ተያይዟል

በናይጄሪያ ሌጎስ የነዳጅ ቦቴ በእሳት ተያይዞ ቢያንስ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የሀገሪቱን ባለሥልጣናት አስታወቁ።

በመኪና ፍሰት በተጨናነቀ መንገድ ላይ ነዳጅ የጫነው መኪና ፍጥነቱን መቆጣጠር አቅቶት ተገልብጦ የጫነው ነዳጅ ከፈሰሰ በኋላ አምስት አውቶብሶችን ጨምሮ 50 መኪኖች በእሳት ተያይዘዋል።

ታላቁ አንዋር መስጊድ ከእሳት ተረፈ

15 ሰዎች በእሳት ቃጠሎ ሕይወታቸውን አጡ

መኪናው ፍሬን እንቢ ብሎት ቦቴው እንደተገለበጠ ተነግሯል።

በአፍሪካ ትልቋ ነዳጅ አምራች በሆነችው ናይጄሪያ የነዳጅ ፍንዳታ የተለመደ ሲሆን ነዳጅ የሚጓጓዘው በአግባቡ ባልተጠገነ መንገድ እና በአገለገሉ መኪኖች ነው።

አደጋው የደረሰው ሐሙስ አመሻሽ ላይ ነው።

Image copyright Getty Images

የፌዴራል መንገዶች ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደገለፀው ከሆነ ነዳጅ የጫነው መኪና ከቁጥጥር ውጭ የሆነውና የተገለበጠው ድልድይ አቅራቢያ ሲደርስ ነው። ከዛም ነዳጅ መፍሰስ እንደጀመረና እሳት ተነስቶ በአቅራቢያው የነበሩ መኪኖች እንደተቃጠሉ ገልፀዋል።

የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሙሃመዱ ቡሃሪ የሰው ልጅ ሕይወት በመጥፋቱ እጅጉን ማዘናቸውን ገልፀዋል።

በመግለጫቸውም ላይ "በቅርብ ጊዜ ካስተናገድነው አሳዛኝ ክስተቶች መካከል አንዱ" ብለውታል።

የመንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት ኬሂንዲ ባሚግቤታን እንዳሉት ከሆነ የነዳጅ ቦቴዎቹ ደኅንነትን ለማስተካከልና ሐላፊነት በሚሰማቸው አሽከርካሪዎች እንዲጓጓዝ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ