በህንድ 11 የቤተሰብ አባላት ራሳቸውን አጥፍተው ተገኙ

የቤተሰቡ መኖሪያ አካባቢ ላይ የነበረው ነገር
የምስሉ መግለጫ,

ቤተሰቡ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ ይኖር እንደነበር ነዋሪዎች ይገልፃሉ

በህንዷ መዲና ደልሂ የአንድ ሰፊ ቤተሰብ አስራ አንድ አባላት ታንቀው መገኘታቸውን አንድ የቤተሰቡ አባል የሆኑ የ70 ዓመት አዛውንት አስከሬን ብቻ ወለል ላይ መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል።

ብዙዎቹ እጃቸው የፍጥኝ ወደ ኋላ የታሰረና አይናቸው በጨርቅ የተሸፈነ እንደሆነና እስካሁን የቤተሰቡ አባላት ህይወት ማለፍ ምክንያት ግልፅ አለመሆኑን ፖሊስ ጠቁሟል።

ግድያም ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬም አለ።

በሌላ በኩል ደግሞ ፖሊስ ቤተሰቡ ምስጢራዊ የሆነ ልማድ እንደነበረው የሚያሳይ ማስረጃ ማግኘቱንም ገልጿል።

ይህ ፖሊስ ቤት ውስጥ አገኘሁት ያለው የፅሁፍ ማስረጃ ቤተሰቡ ይከተል የነበረው ምስጢራዊና መንፈሳዊ ተግባር ከቤተሰቡ አባላት ሕይወት መጥፋት ጋር ግንኙነት እንደሚኖረውም ይጠቁማል።

ፖሊስ ስለ ግድያው ተጨባጭ ነገር ለማግኘት የአስከሬን ምርመራ ውጤት እየጠበቀ ሲሆን ከጎረቤቶች ያገኛቸውን መረጃዎች እንዲሁም አካባቢው ላይ ያለ ሲሲቲቪ ካሜራ ፊልምን በመፈተሽ ላይ እንዳለም አስታውቋል።

አንድ የፖሊስ ባልደረባ ስለ ቤተሰቡ አሟሟት አሁን እንዲህ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ እንደማይቻል ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል።

ሟቾቹ ደልሂ ውስጥ ላለፉት 20 ዓመታት መኖራቸው ተዘግቧል። ሁለት መደብሮች የነበራቸው ሲሆን የቤተሰቡ አባላት ህይወት ማለፍ የታወቀውም እቃ ለመግዛት ወደ መደብሩ ባመሩ ሰዎች ነበር።

የአካባቢው ኗሪዎች ቤተሰቡ ደስተኛና ከሌላው የአካባቢው ህብረተሰብ በፍቅር ይኖር እንደነበር ገልፀዋል።