ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ስብሰባ Image copyright Getty Images

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በመደበኛ ስብሰባው ኦነግ፣ኦብነግና ግንቦት 7 ሽብርተኛ መባላቸው ይሰረዝ ዘንድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የላከለትን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ከተወያየበት በኋላ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ ከዓመታት በፊት እነዚህን የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲሁም አልቃይዳንና አልሻባብን አሸባሪ ማለቱ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ ዛሬ በ2011 ዓ.ም በጀት ላይ የተወያየ ሲሆን በነገው እለት በቀረበለት በጀት ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2011 ዓ.ም በጀት 346 ቢሊየን 915 ሚሊየን 451 ሺህ 948 ብር እንዲሆን ወስኖ ደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል።