በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ የባሌ ጎባ ተወላጆች የኦሮሚያ ባለሥልጣናትን አነጋገሩ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አቤቱታቸውን ሊያሰሙ ከመጡ የጎባ ከተማ ተወላጆች መካከል በከፊል

ቅዳሜ ሐምሌ 14 በባሌ ዞን ጎባ ከተማ በተፈጠረ ግጭት 6 ሰዎች ሕይወታቸውን ካጡ በኋላ ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ወደ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አምርተዋል።

በመቶዎች የሚቆጠሩት እኚህ ግለሰቦች ጥያቄያቸውን ይዘው የኦሮሚያ ክልል የፍትህ ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊን እና ሌሎች ባለሥልጣናትን አነጋግረዋል።

የኮሚቴው ተወካዮች ለቢቢሲ እንደገለፁት ዋና ጥያቄያቸው የኦሮሚያም ሆነ የፌደራል መንግሥት በጎባ የተፈጠረውን ችግር በሚገባ ያውቀዋል ወይ? የሚል እንደነበር ገልፀው ኃላፊዎቹም በአከባቢው የነበረውን የተለየ እንቅስቃሴ ከ15 ቀን በፊት ጀምሮ እየተከታተሉት እንደነበር ገልፀዋል።

በጎባው ግጭት የስድስት ሰዎች ሕይወት ጠፋ

ከምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ጥቃት ጀርባ ያለው ማን ነው?

ኦሮሚያ በአዲስ አበባ በምታገኘው ልዩ ጥቅም ላይ ሊመክር የነበረው ስብሰባ ተበተነ

ኃላፊዎቹ አክለውም በመሃል የቅዳሜው ግጭት እንደተፈጠረ እንደነገሯቸው የኮሚቴው አባላት ለቢቢሲ አስረድተዋል።

ጨምረውም በአካባቢው ከፍተኛ የገንዘብ መጠን መሰራጨቱን የክልሉ የደህንነት መሥሪያ ቤትም እንደሚያውቅ፤ ገንዘቡ ከማን እንደመጣ ለእነማን እንደተበተነ የማጣራት ሥራ እየሰራ እንደሆነ እንደተነገራቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ግጭቱ የብሔርም ሆነ የሐይማኖት እንዳልነበር የሚናገሩት እነዚህ የኮሚቴ አባላት ይህ ግጭት በሌሎች የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው ኃይሎች በገንዘብ የሚደገፍ እንደሆነ እንደሚያምኑ የክልሉ ባለስልጣናትም ይህንን እንዳረጋገጡላቸው ይናገራሉ።

በአሁን ሰዓትም በቂ የመከላከያ ኃይል በስፍራው እንደገባ፣ እነርሱም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተፈጠረውን ነገር በማረጋጋት ሂደት የበኩላቸውን እንዲወጡ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልፀዋል።

ጎባ ሙስሊምና ክርስቲያኑ ተዋዶ የኖረባት ከተማ ናት የሚሉት እነዚህ የኮሚቴ አባላት እነርሱም በግጭቱ ዙሪያ የተለያዩ መረጃዎች እንዳሏቸው ገልፀዋል።

የጎባ የቀድሞ ሰላሟ እንዲመለስ እንፈልጋለን ያሉት በአዲስ አበባ የሚኖሩት የከተማዋ ተወላጆች ይህንን ለማሳየት ዛሬ ወደ ፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት ከመጡት ሰዎች መካከል ሙስሊሞችም እንደሚገኙበት ይናገራሉ።

ሃይ ባይ ያጣው ብሔር ተኮር መፈናቀል

የኮሚቴ አባላቱ ከባለሥልጣናቱ ጋር በነበራቸው ውይይት የኦሮሚያ ክልል የደህንነት ፀጥታ ዋና ኃላፊ እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርን የያዘ የልዑካን ቡድን ወደ ጎባ እንዳመራ እንደተነገራቸው እነርሱም የማረጋጋት ሥራውን እንዲሰሩ መንግሥትም ተሳታፊ የነበሩ ኃይሎችን ህግ ፊት እንዲያቀርብ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልፀዋል።

የኮሚቴው አባላት አሁን ያለውን የመደመር ስሜት የጎባ ልጆችም ማስተጋባት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን በአካባቢው ያሉ ባለስልጣናት የተለያዩ ጫናዎችን እንደሚያደርጉባቸው ተናግረዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ