በወልዲያ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ሁለት ሰዎች ሞቱ

የወልዲያ ማረሚያ ቤት እሳት Image copyright facebook

በወልዲያ ማረሚያ ቤት ትናንት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ሁለት ታራሚዎች ሲሞቱ ሦስቱ ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደረሰ።

ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል አንድ ታራሚ በወልዲያ ሆስፒታል ህክምና አግኝቶ ማታውኑ ሲመለስ አንዱ በሆስፒታል ተኝቶ እየታከመ ይገኛል። ሌላኛው ታራሚ ግን ጉዳቱ ከፍ ያለ በመሆኑ ወደ ደሴ ሆስፒታል ለተሻለ ህክምና ተልኳል በማለት የወልዲያ ማረሚያ ቤት አዛዥ ኮማንደር ፈንታው ደሳለኝ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በወልዲያ እና ፍኖተ-ሰላም ማረሚያ ቤቶች የእሳት አደጋ ደረሰ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ

ዛሬ ማለዳ በድጋሚ ታራሚዎች የምህረት አዋጁ እኛን ለምን አላካተተንም በሚል ግርግር ለማንሳት የሞከሩ መሆናቸውን አንስተው፤ ነገር ግን ገብተው እንዳነጋገሯቸውና አሁን በማረሚያ ቤቶቹ መረጋጋት መታየቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት በቃጠሎው ጉዳት የደረሰባቸውን ቤቶች ጥገና በማድረግ ላይ እንደሆኑም ማወቅ ችለናል።

በተመሳሳይ ትናንት ሐምሌ 18 ቀን 2010 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በመቀሌ ማረሚያ ቤት በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ሁለት እስረኞች መሞታቸውንና ሌሎች መጎዳታቸውን የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር ይትባረክ አለነ ለቢቢሲ እንደገለፁ መዘገባችን ይታወሳል።

በደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት እሳት ተነሳ

በደሴ ከተማ የሸዋበር መስጂድ ላይ በደረሰ ጥቃት ሰዎች ተጎዱ

ማክሰኞ ዕለት ግርግርና ቃጠሎ አጋጥሞት የነበረው የደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤትም በዛሬ ጠዋት የተቃውሞና ግርግር አዝማሚያዎች እንደነበሩና የአካባቢው ሽማግሌዎች ወደ ማረሚያ ቤቱ በመግባት ታራሚዎቹን በማነጋገር ለማረጋጋት ጥረት እንዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ተያያዥ ርዕሶች