የቀድሞዎቹ መሪዎች ኃይለማርያም ደሳለኝና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተገናኙ

የኢትዮጵያ የቀድሞ መሪዎች ኃይለማርያም ደሳለኝና መንግሥቱ ኃይለማርያም Image copyright HAILEMARIAMDESALEGNFACEBOOK

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝና የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በዚምባብዌ መዲና ሃራሬ ተገናኝተዋል።

በርካቶች ሁለቱ ግለሰቦች አንድ ላይ የሚታዩበትን ፎቶግራፍ በማህበራዊ ድረ ገፅ ከተጋሩት በኋላ አቶ ሃይለማሪያም በፌስቡክ ገፃቸው በአገሪቱ ሰላማዊ ሽግግር ከተደረገ በኋላ የቀድሞ የአገሪቱ መሪዎች በተለያየ መልኩ በአገራቸው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ተሳትፎ ቢኖራቸው ምኞታቸው እንደሆነ በመግለፅ ፎቶግራፉን ለጥፈውታል።

ኢህአዴግ ሥልጣን ሲቆጣጠር ወደ ዚምባብዌ የሸሹት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን ለ17 ዓመታት ያህል መርተዋል።

ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በሌሉበት ክስ ተመስርቶባቸው የሞት ፍርድ እንደተፈረደባቸው ይታወሳል።

ሌሎች የደርግ ባለስልጣኖች ከዓመታት እስር በኋላ በምህረት መለቀቃቸውም እንዲሁ ይታወቃል።

ተያያዥ ርዕሶች