በጣልያን 12 አፍሪካውያን ላብ አደሮች በመኪና አደጋ ሞቱ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በጣልያን ብዙ አፍሪካውያን ስደተኞች የሚኖሩት በድህነት ነው
በደቡብ ጣልያን አንድ ሚኒ ባስ እና የጭነት ሚኪና ተጋጭተው 12 አፍሪካዊ የቀን ሰራተኞች መሞታቸው ተሰምቷል።
ሰራተኞቹ ሲሰሩ ከዋሉባቸው የእርሻ ቦታዎች የቡሉጋሪያ መለያ ቁጥር ባለው ሚኒባስ በመመለስ ላይ ነበሩ።
የጭነት መኪናውን ሾፌር ጨምሮ ሌሎች ሶስት ሰዎችም በግጭቱ ተጎድተዋል።
በተመሳሳይ አራት ላብ አደሮች ቅዳሜ ዕለት በመሰል ግጭት ህይታቸውን አጥተዋል።
በርካታዎች ቋሚ ላልሆነ ጊዜ በ"ማፊያ" ቡድኖች የሚቀጠሩ ሰራተኞች ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ክፍያ የሚያገኙ ናቸው።
ከቅዳሜው ግጭት አደጋ በኋላ የእርሻ ላብ አደሮች ህብረት እሮብ ዕለት የስራ ማቆም አድማ ጠርቷል።
ተሳታፊዎች በዕለቱ ቀይ ባርኔጣ አድርገው ፎጊያ ወደ ምትሰኘው ከተማ የእግር ጉዞ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ቀይ ባርኔጣ በፎጊያ ዙሪያ ባሉ ማሳዎች ቲማቲም በመልቀም ሲማስኑ የሚውሉ የቀን ሰራተኞችን የሚወክል ነው።
ከባርነት ወደ ጣልያን የፋሽን ዲዛይነሮች አለም
እኒህ ሰራተኞች 100ኪ.ግ የሚመዝን ቲማቲም ከ1 ዩሮ ባነሰ ክፍያ ነው።