የዚምባብዌ ፖሊስ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን በማደን ላይ ነው

ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን የዚምባብዌ ምርጫን ተከትሎ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን የዚምባብዌ ምርጫን ተከትሎ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል።

ባለፈው ሳምንት በዚምባብዌ የተካሄደውን አወዛጋቢ ምርጫ ተከትሎ ፓሊስ የተቃዋሚውን ኤምዲሲ አሊያንስ ፓርቲ ዘጠኝ አመራሮችን በመፈለግ ላይ ነው።

ምርጫውን ተከትሎ የነበረውን "ህገ-ወጥ" የተቃውሞ ሰልፍ በማነሳሳትም ተወንጅለዋል።

በመዲናዋ ሀራሬ የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ለማስቆም ሠራዊቱ ጣልቃ በመግባቱ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል።

ተቃዋሚው ፓርቲ ኤምዲሲ አሊያንስ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋዋን አሸናፊ ለማድረግ ምርጫው እንደተጭበረበረ ገልፀዋል።

ዚምባብዌ እንዴት ሰነበተች?

ዚምባብዌ ለሙጋቤ ብሔራዊ ቀን ሰየመች

የምርጫው ኮሚሽን በበኩሉ በተቃዋሚው አስተያየት አይስማማም "ፍፁም የሚያጠራጥር ነገር አልነበረም" ብሏል።

የቀድሞው የገንዘብ ሚኒስትርና የፓርቲው አመራር ቴንዳይ ቢቲ በፖሊስ እየታደኑ ካሉ አመራሮች መካከል አንዱ ናቸው።

ቢቢሲ የእሳቸውን የእስር ትዕዛዝ የተመለከተ ሲሆን ቴንዳይ ቢቲ ''ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ" የፓርቲያቸው አመራር የሆኑትን ኔልሰን ቻሚሳን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን አሸንፈዋል ብለዋል የሚል ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ምርጫውን ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎችና የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች በተጋጩበት የተቃውሞ ሰልፍ ላይም ብጥብጥን በማስነሳትም ተከሰዋል።

በድሬዳዋ ከተማ በተከሰተ ግጭት የ10 ሰዎች ህይወት ጠፋ

የኤምዲሲ አሊያንስ ሊቀ መንበር ሞርጋን ኮሚች የፓርቲው የወጣቶች አመራር ሀፒሞር ቺድዚቫና ስድስት ሌሎች የፓርቲው አመራሮችም ፖሊስ እያደናቸው እንደሆነ ለመንግሥት ቅርብ የሆነው ሔራልድ ጋዜጣ ዘግቧል።

ከሮበርት ሙጋቤ የ37 ዓመታት አገዛዝ በኋላ የተደረገው ይህ ምርጫ አገሪቷን ወደ ዲሞክራሲያዊ አቅጣጫ ይመራታል ተብሎ ታምኖ የነበረ ቢሆንም፤ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዋች ባወጣው ሪፖርት ከምርጫ ቅስቀሳው ጀምሮ ተቃዋሚ ፓርቲው ላይ ከፍተኛ የሆነ ጭቆና እንደደረሰበት ነው።

በተለያየ ወቅት የተቃዋሚው ፓርቲ አባላት በወታደሮች ድብደባና እንግልት እንደደረሰባቸውም ሪፖርቱ አትቷል።

በተለያዩ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋን አልመረጣችሁም በሚል በወታደሮች ድብደባ የደረሰባቸውም እንዳሉ የድርጅቱ ሪፖርት በመግለጫው አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሲቡሲሶ ሞዮ ሪፖርቱን "ከእውነት የራቀ" በማለት አስተባብለዋል።

"መንግሥት ስለተከናወነው ድብደባም ሆነ ጠለፋ የሚያውቀው የለም። ከማህበራዊ ሚዲያ የሚመጡ የተሳሳቱ መረጃዎች አሉ " በማለት ለሔራልድ ጋዜጣ ተናግረዋል።

ፖሊስ ከተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ 27 ሰዎችን የከሰሰ ሲሆን፤ በዋስም እንደወጡ ተገልጿል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ