የጦስ አውራ ዶሮ ወጣቶችን አሳሰረ

አውራ ዶሮ

የፎቶው ባለመብት, MyLoupe

ሶስት ጊኒያዊያን ወጣቶች ለሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ያቀረቡት የአውራ ዶሮ ገፀ በረከት ጦስ አምጥቶባቸዋል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ካሶሪ ፎፋና በሀገሪቱ ምስራቃዊ ከተማ ካንካን በተገኙበት ወቅት ነበር ወጣቶቹ የጥቁር አውራዶሮ ስጦታ ያቀረቡት።

የዐይን ምስክሮች እንደተናገሩት ስጦታውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠባቂዎች በፖሊስ ርዳታ ወጣቶቹን በቁጥጥር ስር አውለዎቸዋል።

በአካባቢው ባህል ጥቁር አውራ ዶሮ የመጥፎ ነገር(ሚልኪ) ምልክት ተደርጎ ይታያል። ወጣቶቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ስጦታውን በክፉ ልብ ተነሳስተው እንዳቀረቡ በመታመኑ ሳይሆን እንዳልቀረ ተጠርጥሯል።

ሶስቱ ወጣቶች መሰንበቻውን በፖሊስ ጣቢያ ካሳለፉ በኋላ በዛሬው ዕለት ከእስር ተፈተዋል።