የቢቢሲ አማርኛ በአንድ ዓመት ውስጥ ያቀረባቸው ተነባቢ ዘገባዎች

የቢቢሲ አማርኛ በአንድ ውስጥ ያቀረባቸው ተነባቢ ዘገባዎች
የምስሉ መግለጫ,

የቢቢሲ አማርኛ በአንድ ውስጥ ያቀረባቸው ተነባቢ ዘገባዎች

ቢቢሲ አማርኛ ዜናና ትንታኔዎችን ማቅረብ ከጀመረ እነሆ አንድ ዓመት ሆነ። በዚህ ወቅትም በሃገሪቱ በርካታ ጉልህ ክስተቶች ተመዝግበዋል። በተለያዩ ስፍራዎች ተቃውሞ የተከሰተበት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተላልፎ የተነሳበት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን የለቀቁበት፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት፣ እስረኞች የተፈቱበት፣ ለሁለት አስርት ዓመታት ተፋጠው የነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ሰላም የመጡበት ዓመት ነበር።

በዚህ በርካታ ክስተቶች በተከናወኑበትና የለውጥ ዓመት በነበረው 2010 ዓ.ም የቢቢሲ አማርኛ አስር ተነባቢ የነበሩ ፅሁፎች የሚከተሉት ነበሩ።

1. አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ - በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት አቶ በረከት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስገብተዋል። አቶ በረከት ስምኦን ለበርካታ ዓመታት በቦርድ ሰብሳቢነት ሲመሩት ከነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሊለቁ እንደሆነ ተነግሯል።

 • የታተመበት ቀን ጥቅምት 6/2010
 • የአንባቢ ብዛት 57 166

2. 40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ- ማንነታቸው ያልታወቀ 40 የታጠቁ ወታደሮችን ይዞ ትግራይ ክልል የገባ አንቶኖቭ አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ።

 • የታተመበት ቀን ሐምሌ 24/2010
 • የአንባቢ ብዛት 45 515

3. መንግሥቱ እና የኮሎኔል አጥናፉ ኑዛዜ- ኮ/ል መንግሥቱ ደርግን ኮትኩተው አሳድገውት ይሆናል። ነገር ግን አልወለዱትም። የደርግ እናትም አባትም ኮ/ል አጥናፉ ናቸው። ሆኖም ደርግ ፈጣሪውን መልሶ ለመብላት የወሰደበት ጊዜ ከ5 ዓመት ያነሰ ነበር፡፡ ኅዳር 3/ 1970 በዕለተ ቅዳሜ አጥናፉ ተገደሉ። "አብዮት ልጆቿን በላች" ተባለ።

 • የታተመበት ቀን ግንቦት 10/2010
 • የአንባቢ ብዛት 37 387

4.ስለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን? - የታላቁ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ ከተገኘ በኋላ እሰካሁን ያገኘናቸው አስር የተረጋገጡ መረጃዎች።

 • የታተመበት ቀን ሐምሌ 19/2010
 • የአንባቢ ብዛት 36 581

5.አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ - የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር መዋላቸው፣ ከስልጣን ከመውረዳቸው በፊት ከአቶ አብዲ መግለጫ ውስጥ የበርካቶችን ትኩረት የሳበው የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋን በሚመለከት የሰጡት አስተያየትና ከስልጣን መውረዳቸው ተነባቢነትን አግኝቷል።

 • የታተመበት ቀን ነሐሴ 1/2010
 • የአንባቢ ብዛት 31 342

6. ጀዋር መሐመድ ከ"ቲም ለማ" ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት ነበረው? - አሁን ካሉት አመራሮች ጋር በትግሉ ወቅት የቀደመ ትውውቅና ግንኙነት ስለመኖሩ የተጠየቀው ጀዋር ቀጥተኛ ምላሽ ለመስጠት ባይፈቅድም አሁን ያለው አመራር ወደፊት ገፍቶ እንዲመጣ ውስጥ ውስጡን ላለፉት ዐሥርታት በደኅንነትም በወታደራዊ ክንፍ በርካታ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ለቢቢሲ ተናግሯል።

 • የታተመበት ቀንሐምሌ 27/2010
 • የአንባቢ ብዛት 28 269

7. ብሔርን ከመታወቂያ ላይ ማስፋቅ. . . - ብሔር መታወቂያ ላይ መካተቱን ከሚቃወሙት አንዱ የፊልም ባለሙያ የሆነው ያሬድ ሹመቴ ይህንን ለማስቀየር ብዙ እርቀት ተጉዟል። "ብሔር ለሚለው ሀሳብ ለኔ ኢትዮጵያ የምትለው ትበቃኛለች" በማለትም ይናገራል።

 • የታተመበት ቀን መስከረም 15/2010
 • የአንባቢ ብዛት- 27 803

8.አቶ አብዲ ስለተናገሩት ጉዳይ እንደማያውቅ ኢህአዴግ ገለፀ - የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መሰተዳደር የሆኑት አቶ አብዲ ሞሃመድ ከክልላቸው የመገናኘ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሯቸው ነገሮች አነጋጋሪ ሆኗል።

• የታተመበት ቀን ሐምሌ 5/2010

 • የአንባቢ ብዛት -26 117

9.ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? - በ1997 የኢትዮጵያ ምርጫ የአውሮፓ ምርጫ ታዛቢ የነበሩት አና ጎሜዝ ዲፕሎማቶች የተፈጠሩት እንዲዋሹ አይመስለኝም። ዝም አልልም፤ ለምን ዝም እላለሁ ይላሉ።

 • የታተመበት ቀን ነሐሴ 25/2010
 • የአንባቢ ብዛት 25 921

10."አቶ በረከት ባለሐብቶችን ለቅመህ እሰር ብሎኝ ነበር" አቶ መላኩ ፈንታ - የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ በከፍተኛ ሙስና ክስ ተመስርቶባቸው ለአምስት ዓመታት የታሰሩ ሲሆን ከእስር የተለቀቁት ከጥቂት ወራት በፊት ነው። በቀድሞ ፓርቲያቸው ብአዴን ውስጥ እየተወሰደ ስላለው እርምጃና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

 • የታተመበት ቀን ነሐሴ 25/2010
 • የአንባቢ ብዛት 23 464