ኢትዮጵያ በውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ብዛት ቀዳሚ ሆነች

ተፈናቃይ Image copyright Nashon Tado/NRC
አጭር የምስል መግለጫ በምግባረ ሰናይ ድርጅቶች የሚከፋፈሉ የዕርዳታ ቁሶችን ለማገኘት ተፈናቃዮች እሰከ 50 ኪ.ሜ ድረስ በእግር መጓዝ ሊጠበቅባቸው ይችላል።

ባለፉት ስድስት ወራት ኢትዮጵያ በሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ብዛት ከዓለም ቁጥር አንድ መሆኗ ተነገረ።

ዓለም አቀፉ የሃገር ውስጥ ተፈናቀዮች ተቆጣጣሪ ማዕከል (ኢንተርናሽናል ዲስፕለስመንት ሞኒተሪንግ ሴንተር) እንደሚለው ከሆነ የ2018 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለደህንነታቸው በመስጋት የመኖሪያ ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል።

''1.4 ሚሊዮን ህዝብ ግጭት በመሸሽ የመኖሪያ ቀዬውን ጥሎ ሲሰደድ በቂ ትኩረት አልተሰጠውም። የተቀረው ዓለም የኢትዮጵያን ችግር ማየት አልፈቀደም'' በማለት የኖርዌ የስደተኞች ካውንስል የቀጠናው ዳይሬክተር ኒገለ ትሪክስ ተናግረዋል።

በጉጂ እና ጌዲዮ ግጭት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ

"የጌዲዮና ጉጂ ተፈናቃዮች ቸል ተብለዋል" የዓለም ቀይ መስቀል ማኀበር

በችግር ላይ የሚገኙት ተፈናቃዮች

በጌዲዮ እና ምዕራብ ጉጂ የተከሰቱት ግጭቶች እንዲሁም በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ ድንበር ላይ የተከሰቱት ተደጋጋሚ ግጭቶች በሃገር ውስጥ የተፈናቀሉትን ሰዎች ቁጥር 1.4 ሚሊዮን እንዳደረሱት ሪፖርቱ ይጠቁማል።

የኢትዮጵያ መንግሥት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለተፈናቀዮች ምላሽ ለመስጠት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ፤ ይሁን እንጂ ከተፈናቀዮች ከፍተኛ ቁጥር አንጻር ያለው ፍላጎትና ዝናባማው የአየር ሁኔታ ችግሩን ከመንግሥት እና ከበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ አቅም ባላይ እንዳደረገው ሪፖርቱ ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ እየሰራ ነው። መንግሥት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተፈናቃዮችን ወደ ቀደመ መኖሪያቸው ለመመለስ ቅድሚያ ሰጥተው እየሰሩ ነው። በዚህም ተፈናቀዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው። ይሁን እንጂ አሁንም በርካቶች ቤታቸው እንደወደመ ነው፤ ይላል ሪፖርቱ።

''ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ ቢፈልጉም ከመኖሪያቸው ሲሰደዱ ባዶ እጃቸውን ነው ይወጡት። ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚደረግበት መንገድም በራሳቸው ፍቃድ እና ደህንነታቸው ተረጋግጦ አንዲሁም አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው ሊሆን ይገባል'' ሲሉ ትሪክስ ይናገራሉ።

ተያያዥ ርዕሶች