ቪየትናም ነዋሪዋቿ የውሻ ሥጋ እንዳይበሉ እያሳሰበች ነው

ቪየትናም ነዋሪዋቿ የውሻ ስጋ እንዳይበሉ እያሳሰበች ነው Image copyright Getty Images

የቪየትናም ባለሥልጣናት የሃገሪቱ ነዋሪዎች፤ በተለይ የርዕሰ መዲናዋ ሃኖይ ሰዎች የውሻ ሥጋ እንዳይበሉ በማሳሰብ ላይ ይገኛሉ። የከተማዋን ስም ያጠለሻል የሚል ነው ምክንያታቸው።

የሃኖይ ሕዝቦች ኮሚቴ እንዳስታወቀው የውሻ ሥጋ መብላት ዘመናይ የሆነችውን ከተማ ስም ከማቆሸሹም በላይ ለበሽታ ሊዳርግ ይችላል።

በሃኖይ ከተማ የሚገኙ አንድ ሺህ ያህል ሱቆች የውሻ እና የድመት ሥጋ በሰልፍ ይሸጥባቸዋል።

ትራምፕ ቪየትናም ገብተዋል

ኮሚቴው የውሻ ብቻ ሳይሆን የድመት ሥጋ መብላትም እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል፤ ምንም የውሻን ያህል ተወዳጅነት ባይኖረውም።

ከስም ማቆሸሹና ከበሽታው በዘለለ የቤት እንስሳቱ በግፍ መገደል ድርጊቱ እንዲቆም ለማድረግ ያስገድደናል ብሏል ኮሚቴው።

የቢቢሲ ቪየትናም ዝግጅት ክፍል ባልደረባ የሆነው ሊን ጉየን «ምንም እንኳ አብዛኛው የሃገሪቱ ሰው ውሻ መብላትን ባይቀበለውም አሁንም ተመጋቢው በርካታ ነው» ሲል ስለሁኔታው ይናገራል።

ለማነፍነፍ የሰነፈችው ጥሩ ውሻ

ወሬውን የሰሙ ብዙዎች 'መልካም ዜና' ነው ቢሉም የተቃወሙት ግን አልጠፉም፤ 'ባህልችንማ' በሚል።

«የውሻ ሥጋን አትብሉ ብሎ መከልከል ነፃነትን እንደመግፈፍ ነው» ሲል እንድ ቪየትናማዊ ሃሳቡን በፌስቡክ ገልጿል።

«ባይሆን ቀረጥ መጨመርና በተወሰኑ ሥፍራዎች ብቻ እንዲሸጥ ማድረግ» ሲልም አማራጭ ሃሳብ አቅርቧል።

የቪየትናም ዋና ከተማ ሃኖይ 490 ሺህ ያህል ውሾችና ድመቶችን በቤት እንስሳነት ታስተዳድራለች።

ካለሁበት 27፡ 'እንጀራ ከበላሁ ዓመት አልፎኛል'

ተያያዥ ርዕሶች