የረቡዕ ምሽት አጫጭር ዜናዎች

አጭር የምስል መግለጫ በካናዳ ሎተሪ የደረሰው አፍሪካዊው ስደተኛ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር በላቸው መኩሪያ የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ።

ምክንያታቸው ከሃገር ውጪ የሚገኙትን የቤተሰብ አባላቶቻቸውን ለመቀላቀል ከሃገር ሊወጡ በመሆኑ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በሌላ ዜና

ኢትዮጵያ በሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ብዛት ከዓለም ቁጥር አንድ መሆኗ ተነገረ።

ዓለም አቀፉ የሃገር ውስጥ ተፈናቀዮች ተቆጣጣሪ ማዕከል የ2018 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለደህንነታቸው በመስጋት የመኖሪያ ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል።

በተፈናቃዮች ብዛት ኢትዮጵያ ከዓለም ቀዳሚ ሆነች

ድንበር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለቀው ይወጣሉ

ሊቢያ

በሊቢያ ብቸኛው የአየር ማረፊያ አገልግሎት መስጠት በጀመረ በሁለት ቀናት ውስጥ በረራዎችን ሰረዘ።

ይህ የሆነው ትሪፖሊ የሚገኘው ሚቲጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ማክሰኞ ምሽት በደረሰበት የሮኬት ጥቃት ሳቢያ ነው።

በጥቃቱ የደረሰ ጉዳት ስለመኖር አለመኖሩም የተባለ የለም።

ያልተጠበቁ ክስተቶች የታዩበት ዓመት

አፍሪካ

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚደንት ጂን ክላውዴ ከአፍሪካ ጋር በኢንቨስትመንትና በስራ ፈጠራ ያላቸውን ትስስር ማጎልበት እንደሚሹ አስታወቁ።

ዕቅዱ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በአፍሪካ 10 ሚሊየን የሚደርሱ የስራ ዕድሎችን መፍጠርን ያካትታል።

በተያያዘ ዜና

የአውሮፓ ህብረት ከአፍሪካና ከሌሎች አካባቢዎች የአውሮፓን ድንበር አቋርጠው የሚገቡ ስደተኞችን ለመከላከል 10 000 ወታደሮችን በድንበሮች አካባቢ ሊያሰማራ መሆኑ ተገጿል።

በምትኩ ዜጎቹ በትውልድ አገራቸው እንዲቆዩ ለማድረግ 'ያለፈበት' ያሉትን የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል።

'ደራሲ ያደረገኝ ማኅበራዊ ሚዲያው ነው'

ካናዳ

አፍሪካዊው ስደተኛ በካናዳ በአምስት ወር ጊዜ ውስጥ ሁለት ጊዜ የሎተሪ ዕጣ አሸነፈ።

አንድ ላይ በገዛቸው ሁለት የሎተሪ ትኬቶች 2.7 ሚሊየን ዶላር ና 2.1 ሚሊየን ዶላር በድምሩ 3.5 ሚሊየን ዶላር በማሸነፍ ቱጃር ሆኗል።

አፍሪካዊው ስደተኛ በአሁኑ ሰዓት ዊኒፔግ፣ ማኒቶባ የሚኖር ሲሆን ሽልማቶቹን የራሱን የንግድ ተቋም፤ የነዳጂ ማደያ አሊያም የመኪና እጥበት ስራ እንደሚከፍትበት ተናግሯል።

እንዲሁም ለትምህርት እንደሚያውለው ገልጿል።

ከአንታርክቲካ በስተቀር ስድስቱን አህጉሮች ያዳረሰችው ኢትዮጵያዊት

ህንድ

ባለፈው ሳምንት የሕንዱ የሐይድራባድ ንጉሥ የሆነውን በአልማዝ ያጌጠ የወርቅ ምሳ እቃ የሰረቁት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ዘራፊዎቹ የምሳ እቃውን ከሰረቁ በኋላ ወደ ሌላ ከተማ በመሄድ ዘመነኛ ሆቴል ሲዝናኑ ነበር።

በወርቁ የምሳ ዕቃም ምግብ እንደተመገቡበት የህንድ ፖሊስ አስታውቋል።

2010 ለታምራት ላይኔ፣ ለእስክንድር ነጋ፣ ለሃጫሉ ሁንዴሳ . . .

ቪየትናም

የቪየትናም ባለሥልጣናት የሃገሪቱ ነዋሪዎች የውሻ ሥጋ እንዳይመገቡ አሳሰቡ።

የሃኖይ ሕዝቦች ኮሚቴ እንዳስታወቀው የውሻ ሥጋ መብላት ዘመናዊ የሆነችውን ከተማ ስም ከማቆሸሹም በላይ ለበሽታ ሊዳርግ ይችላል ብለዋል።

በሃኖይ ከተማ የሚገኙ አንድ ሺህ ያህል ሱቆች የውሻ እና የድመት ሥጋ በሰልፍ ይሸጥባቸዋል።

የ2010 የጥበብ ክራሞት

ጤና

የካንሰር በሽታ ስርጭት በአለም አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ መምጣቱን አንድ ጥናት አመለከተ።

በዚህ ዓመት ብቻ 18 ሚሊየን ገደማ ሰዎች በካንሰር ሲጠቁ ከ9 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ህይወታቸውን አጥተዋል።

በድህነታቸው ከሚጠቀሱት አገራት ይልቅ ሐብታምና ያደጉ የሚባሉት አገሮች በኑሮ ዘይቤያቸው ምክንያት ለካንሰር የመዳረጋቸው እድል ከፍተኛ ነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ