ግንቦት ሰባትና አርበኞች ግንባር አልተለያዩም ተባለ

የአርበኞች ግንቦት 7 አርማ Image copyright AG7

ከሰሞኑ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነት እና ለዲሞክራሲ ንቅንቄ አካል የሆነው እና የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ከፓርቲው ሊለያይ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል።

የፓርቲው ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ግን ይህንን "የተለመደ የማኅበራዊ ሚዲያ" አሉባልታ ነው ብለውታል።

"ወደአገር ቤት ስንመጣ የመጣው ፓርቲ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነት እና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ነው። አርበኞች ግንቦት ሰባት የሚባል ነገር የለም፤ የኢትዮጵያ አርበኞች ንቅናቄ የሚባል የለም። ከውስጥ ተገንጥሎ ሊወጣ የሚችል አካል የለም። ተዋኽደናል" ሲሉ አቶ ኤፍሬም ለቢቢሲ ገልፀዋል።

"ሰው እየሳቀ መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ ነበር ያልኳቸው'' አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ

ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው

ኦህዴድ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ታሪክ ሊያደርጋቸው ይሆን?

ለበርካታ አመታት በኢትዮጵያ መንግስት የሽብር ዝርዝር ውስጥ ተቀምጦ የነበረው የአርበኞች ግንቦት ሰባት መቀመጫውን በጎረቤት ኤርትራ አድርጎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን መምጣት በኋላ በአገሪቱ የተከናወኑ ለውጦችን ተከትሎ ቡድኑ የትጥቅ ትግሉን ማቆሙን ይፋ ካደረገ በኋላ ከሌሎች መሰል ቡድኖች ጋር ከሽብር ዝርዝር መሰረዙ ይታወሳል።

የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች በቅርቡ ወደአገር ቤት ሲመለሱ በመዲናዋ አዲስ አበባ ሞቅ ያለ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፥ አቶ ኤፍሬም ፓርቲያቸው ወደኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ ከዚህ በፊት በህቡዕ ይንቀሳቀሱ የነበሩ አባሎቻቸውን ከአመራሩ ጋር በማስተዋወቅ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

"እንኳን መለያየት ይቅርና፥ አርበኞች ግንቦት ሰባት ከዛሬ ሁለት ወር በፊት ከነበረውም በተሻለ ጥንካሬ ላይ ይገኛል" ብለዋል።

በስልክ ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑትና ይህንን ውሳኔ ለማሳለፍ በጎንደር የተካሄደውን ስብሰባ መምራታቸውን ያስረዱት አርበኛ መንግስቱ ወ/ስላሴ ጉዳዩን በተመለከተ በሚቀጥለው እሁድ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ገልፀው መለያየቱ ግን ዕውን መሆኑን ነግረውናል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ