በቡራዩ ጥቃት የተጠረጠሩ ፍርድ ቤት ቀረቡ

የፍርድቤት መዶሻ Image copyright Mark Metcalfe

በቡራዩ ከተማና አካባቢዋ በተፈፀመው ጥቃት እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ተጠርጣሪዎቹ በቡራዩ የወረዳ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ነው የቀረቡት።

ቁጥራቸው በርካታ የሆኑት ተጠርጣሪዎቹ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

መርማሪ ፖሊስ እንዳስታወቀው ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች በሰዎች ሕይወት ማለፍ፣ በከባድና ቀላል የአካል ጉዳት በማድረስ፣ በንብረት ውድመት እና ዘረፋ የተጠረጠሩ ናቸው።

በቡራዩ ጥቃት ፈጻሚዎቹ የባንክ ሂሳብ ውስጥ 8 ሚሊዮን ብር ተገኘ፡ ዶ/ር ነገሪ

ሞትና መፈናቀል በአዲስ አበባ ዙሪያ

ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው

ችሎት ፊት በቀረቡት ተጠርጣሪዎች ላይም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የጠየቀ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም የተጨማሪ ጊዜውን ፈቅዷል።

ከቀናት በፊት በቡራዩ እና አካባቢዋ ጥቃት ፈጽመዋል ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉ ግለሰቦች የባንክ አካውንት ውስጥ 8 ሚሊዮን ብር መገኘቱን የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ዶ/ር ነገሪ የፖለቲካ ዓላማ ለማሳካት ገንዘብ በመመደብ የሕብረተሰቡን ሰላም ለማወክ ከአዲስ አበባ ጀምሮ የተንቀሳቀሰ ቡድን አለ ብለው ነበር።