ዶ/ር ዐብይ አህመድ የኦዴፓ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

አዲሱ አርማ Image copyright OPDO Official FB

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) በጅማ ከተማ ከረቡዕ ዕለት ጀምሮ ሲያካሂድ በነበረው ድርጅታዊ ጉባዔ ዶ/ር ዐብይ አህመድን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ በመምረጠ አጠናቀቀ።

አቶ ለማ መገርሳ ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተሰይመዋል።

ሊቀመንበሩ እና ምክትል ሊቀመንበሩ እስከቀጣዩ ጉባዔ ድረስ ኦዴፓን እንደሚመሩ ተገልጿል።

ፓርቲው ዘጠኝ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንዲሁም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን መምረጡም ታውቋል።

የፓርቲው ጉባዔ ትናንት በእጩነት ከቀረቡት ስድሳ አባላቱ መካከል ሃምሳ አምስቱን ዛሬ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሰይሟል።

ኦዴፓ ጉባዔውን ከመጀመሩ በፊት ሲል እንደነበረው ከሃምሳ አምስቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በርካታ አዳዲስና ወጣት አባላት እንደተካተቱበት ለማወቅ ተችሏል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ኦዴፓ ስሙን፣ አርማውን፣ ህገ ደንቡን፣ አመራሩን፣ አመለካከቱንና አደረጃጀቱን፤ የ21ኛው ከፍለ ዘመን የሚጠይቀውን አመራር ለመስጠት በሚያስችል መልኩ በመማዋቀር ዘጠነኛ ጉባዔው በድል መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ድርጅቱ የተማሩ፣ ለመማር የተዘጋጁና ብቃት ያላቸው ወጣቶች ወደፊት በማምጣት ስያሜውን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ወደፊት የሚያራምድ በመሆኑ፤ ሌሎች ለኢትዮጵያ ህዝቦች የሚታገሉ በሙሉ ከኦዴፓ ትምህርት ሊወስዱ ይገባል ብለዋል።

በቅርቡ በደቡብ ክልል ንብረትንና ጥቃትን በባህላቸው መሠረት የተከላከሉ የጋሞ ሽማግሌዎች ያደረጉትን ገድል አድንቀዋል።

በመጨረሻም ምርጫው ዲሞክራሲያዊ እና የተሳካ እንደነበር ገልጸዋል።

ኦህዴድ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ታሪክ ሊያደርጋቸው ይሆን?

ኦህዴድ ስሙና አርማውን ቀየረ

ከእነዚህም ውስጥ ዶክተር ዐብይ አህመድ (ጠቅላይ ሚኒስትር)፣ አቶ ለማ መገርሳ (የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት)፣ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ (የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር)፣ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ (ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ)፣ ኢንጂነር ታከለ ኡማ (የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ)፣ ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን (የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት) ሲገኙበት።

በተጨማሪም አቶ አዲሱ አረጋ (የፓርቲው ከፍተኛ ባለስልጣን)፣ ዶክተር ግርማ አመንቴ (ሚኒስትር)፣ አቶ ታዬ ደንደአ (የዐቃቤ ህግ ቃል አቀባይ)፣ አቶ ካሳሁን ጎፌ (መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ)፣ አቶ አህመድ ቱሳ (የቀድሞ ሚኒስትር)፣ አቶ አብዱልአዚዝ መሃመድ (የሜቴክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር) እና ሌሎችም ተካተውበታል።

ፓርቲው ትናንት በርካታ መስራችና ነባር አባላቱን ያሰናበተ ሲሆን አዲስ የተተኩትም የተሰናባቾቹን ቦታ የያዙ ናቸው። በተጨማሪም ኦዴፓ አዲስ ስያሜና አርማን ይፋ አድርጓል።