ኬንያዊው ባለሥልጣን ነብሰ ጡር ጓደኛውን በማስገደል ወንጀል ተከሷል

ነብሰ ጡር ጓደኛውን ያስገደለው ኬንያዊ ባለሥልጣን Image copyright EPA

ኦኮት ኦባዶ የተባሉት ኬንያዊ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከትዳራቸው ውጪ ግንኙነት የነበራቸውን ነብሰጡር ጓደኛቸውን በጭካኔ እንድትገደል አዘዋል እንዲሁም አስተባብረዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

ባለሥልጣኑ ይህን ድርጊት አልፈፀምኩም በማለት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

የሻሮን ኦቲየኖ ሬሳ ጫካ ውስጥ ከተገኘ በኋላ ነው ሁኔታው ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ከበርካቶች ጫና መበርታት የጀመረው።

ቻይናዊው በዘረኛ ንግግሩ ምክንያት ከሃገር ሊባረር ነው

የአስከሬን ምርመራው እንዳረጋገጠው የ26 ዓመቷ ሻሮን ተደፍራ እና በስለት 8 ቦታ ተወግታ ነው የተገኘችው፤ ሽሉም በጥቃቱ ጊዜ ሕይወቱ እንዳለፈ ተረጋግጧል።

ሚጎሪ የተሰኘው የኬንያ ግዛት አስተዳዳተሪ የሆኑት እኚህ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ሲሆን ክሱ ወደ ፍርድ ቤት ተልኳል።

የፍርድ ቤቱ ዳኛ ባልሥልጣኑ ብቻ ሳይሆኑ ሁለት አጋሮቻቸው በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ አዘዋል፤ አንዱ በግድያ ሌላኛው ደግሞ በማስተባበር ወንጀል ተጠርጥረው።

አቃቤ ሕግ ሻሮን እና ሃገረ ገዢ ኦባዶ የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው አረጋግጫለሁ ብሎ እርግዝናው ግን ያልተፈለገ ነው፤ በተለይ ደግሞ በተጠርጣሪ በኩል ሲል አክሏል።

ጉግል ኢንተርኔትን በላስቲክ ከረጢት ይዞ ኬንያ ገብቷል

የሟች እና የተጠርጣሪው ኦባዶ ግንኙነት ሃገር ያወቀው፤ ፀሐይ የሞቀው ነው በተለይ ደግሞ ባለሥልጣኑ በሚያስተዳድሩት አካባቢ ሲል አቃቤ ሕግ ጉዳዩን አብራርቷል።

የሃገር ገዢው ኦባዶ ባለቤት የባላቸውን ከትዳር ውጭ የተመሠረት ግንኙት እያወቁት ባለሥልጣኑ ይህን ድርጊት መፈፀማቸው ደግሞ ክሱን ያከብደዋል ይላል አቃቤ ሕግ።

በርካታ ኬንያዊያንን ያስቆጣው ይህ ድርጊት በቅርብ ቀን ፍርድ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ኬንያ ሺሻን አገደች

ተያያዥ ርዕሶች