የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ብሬት ካቭና የፍርድ ቤት ውሎ

የትራምፕ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዕጩ የፍርድ ቤት ውሎ Image copyright Getty Images

በአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኃለቃነት ከወራት በፊት የታጩት ዳኛ ብሬት ካቭና በወሲባዊ ጥቃት ተጠርጥረዋል።

ጉዳዩ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን አፍ ማሟሻ ከሆነ ቢሰነባብትም በስተመጨረሻ ወደ ሃገሪቱ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት ደርሷል።

ጥቃቱን አድርሰዋል የተተባሉት ዕጩ ብሬት እና ወሲባዊ ጥቃት ደርሶብኛል ያሉት ዶ/ር ክርስቲን ብላሲ ፎርድ በሴናቶሮች ፊት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዳኛ ብሬት ካቭና ወሲባዊ ጥቃቱን አልፈፀምኩም ሲሉ ስሜታዊነት በተሞላበት መልኩ ክሱን አጣጥለዋል።

የሰሞኑ የአዲስ አበባ እስርና ሕጋዊ ጥያቄዎች

ከሳሽ ዶ/ር ክርስቲን ፎርድ በበኩላቸው ሰውየው ከ30 ዓመታት በፊት ያደረሱባቸው ወሲባዊ ጥቃት ሕይወታቸውን ክፉኛ እንዳመሳቀለው አስረድተዋል።

የጎንደር ሙስሊሞች እና የመስቀል በዓል

ፕሬዝደንት ትራምፕ ብሬት 'ሃቀኛ' ናቸው ሲሉ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት በዕጩነት ያቀረቧቸውን ሰው ደግፈው ታይተዋል።

ፕሬዝደንት ትራምፕ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ሴናተሮች 'አጥፊ' የሆነ ዕቅድ የኮነኑ ሲሆን የተከሳሽን መልካም ስም እያጎደፉ ነው ሲሉም ወቀሳ ሰንዝረዋል።

የሴናተሮች ሕግ ተርጓሚ ኮሚቴ በብሬት ካቭና ዕጩነት ዙሪያ ድምፅ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ይዟል፤ ምንም እንኳ ሪፐብሊካኑ ሙሉ በሙሉ ለሰውየው ድምፃቸውን መስጠታቸው ቢያጠራጥርም።

ጠቅላላ ሴናተሮች በሚቀጥለው ሳምንት አጋማሽ ተሰባስበው በሰውየው ዕጣ ፈንታ ላይ ውሳኔ እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል።

የ51 ዓመቷ ዶ/ር ክርስቲን ፎርድ እንባ እየተናነቃቸው ነበር ቃላቸውን ለምክር ቤቱ አባላት ያሰሙት።

በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር ዘጠኝ ደርሷል ተባለ

«እዚህ የተገኘሁት ወድጄ አይደለም» ሲሉ የተደመጡት ዶ/ር ክርስቲን «ፍራቻ ውስጥ ነኝ፤ እዚህ የተገኘሁት የዜግነት ግዴታዬን ለመወጣት ነው፤ ብሬት እና እኔ ትምህርት ቤት እያለን የገጠመኝን ለሁሉም ለማሳወቅ ነው» ሰሉ አክለዋል።

ከሳሽ የ15 ዓመት ታዳጊ ሳሉ የ17 ዓመቱ ብሬት እና ጓደኛው መኝታ ቤት ውስጥ ቆልፈውባት ልብሷን በማወላለቅ ሊደፍሯት እንደሞከሩ እና እንደተሳለቁባት ቃላቸው ሰጥተዋል።

ጉዳዩ ከበርካታ ዓመታት በፊት ስለሆነ ምናልባት ተሳስተው ከሆነ ተብለው ሲጠየቁ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሲሉ ተናግረዋል።

ተከሳሽ በበኩላቸው «እኔ ዶ/ር ክርስቲንንም ይሁን ሌላ ሰው ላይ ወሲባዊ ጥቃት አላደርስኩም» ሲሉ ክሱን ክደዋል።

ከሳሽ ባስቀመጡት ቦታ ላይ አለመገኘታቸውን ነው ለሴናተሮቹ ያሳወቁት።

ቢል ኮዝቢ ወደ ዘብጥያ ወረዱ

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ