የዘጠኝ አመቷ ታዳጊ "ሕይወት በቃሽ" ተባለች

ታዳጊዋ ፓይተን ሰመንስ Image copyright Tiffany Hofstetter

የዘጠኝ ዓመቷ ፓይተን ሰመንስ በህይወትና በሞት መካከል ነች። በእርግጥ በሳይንሳዊ አገላለጽ አዕምሮዋ መስራት ስላቆመ ('ብሬን ዴድ' በመሆኗ) አለች ለማለት ይቸግራል። የምትገኘውም በማሽን ድጋፍ ነው።

ሆኖም የአሜሪካ፣ ቴክሳስ ፍርድ ቤት በማሽን መታገዟን እንድታቆም ውሳኔ አስተላልፏል። በፍዱ መሰረት ከማሽን እርዳታ ወጥታ ህይወቷ ያቆማል ማለት ነው።

የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ

"ለወታደራዊ ደኅንነቱ የማንቂያ ደወል ነው"

ዋሺንግተን ስቴት የሞት ቅጣትን አገደች

ታዳጊዋ ልቧ በአግባቡ መምታት ባለመቻሉ የደም ዝውውሯ ተገትቷል። ባለፈው ወር ቤተሰቦቿ ወደ ፍርደ ቤት ሄደው በማሽን ታግዛ እንድትቆይ አስፈቅደው ነበር።

ፍርድ ቤቱ እንደሚለው፤ ቤተሰቦቿ ካስፈቀዱት ለተጨማሪ ጊዜ በማሽን ታግዛ እንድትቆይ የሚያስችል ማስረጃ አልቀረበለትም። ከዚህ ቀደም ቤተሰቦቿ ያቀረቡት ጥያቄ ታዳጊዋን ሊያዘልቅ የሚችለው እስከፊታችን ሰኞ ብቻ ነው።

የቤተሰቡ ጠበቃ ጀስቲን ሙር እንደሚሉት፤ ቤተሰቡ ለተጨማሪ ጊዜ በማሽን እንድትቆይ ፍቃድ ለመጠየቅ አልወሰነም።

ቤተሰቦች በዚህ አይነት መንገድ በፍርድ ቤት ውሳኔ አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ እንዳይገቡ ሕጉን በጥልቀት መመርመር እንደሚያሻም አስረድተዋል።

ዶክተሮች በማሽን ከመታገዝ ውጩ አማራጭ እንደሌላት ውሳኔ ላይ የደረሱት ታዳጊዋ መተንፈስ ተስኗት ወደ ህክምና ከሄደች በኋላ ነበር።

በቴክሳስ ህግ መሰረት የአንድ ሰው አዕምሮው መደበኛ ስራውን ማከናወን ከተሳነው ግለሰቡ እንደሞተ ይቆጠራል። የፓይተን ቤተሰቦች ልጃቸውን በማሽን እንድታገዝ ፍርድ ቤት የጠየቁት ወደሌላ ህክምና መስጫ መውሰድ እስኪችሉ ነበር።