ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጥያቄያቸውን ያቀረቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ይቅርታ መጠየቃቸውንና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች ያንብቡ

Image copyright Office of the deputy Prime Minister

ኢትዮጵያ

• ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጥያቄያቸውን ያቀረቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ይቅርታ ጠየቁ። ከትናንት በስቲያ ቤተ መንግስት በመሔድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ጥያቄ ያቀረቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ይቅርታ እንደጠየቁ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ጥያቄያቸው ትክክለኛና ተገቢ ቢሆንም ያቀረቡበት መንገድ ግን ህግና ስርዓትን ያላከበረ እንደሆነም ከኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ እና ከኢፌዲሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ጋር ባደረጉት ውይይት እንደተጠቀሰም ተገልጿል።

ጥያቄያቸውን ያቀረቡት የሁለተኛ ክፍለ ጦር ሬጅመንት አባላት ከሀገሪቱና ከመከላከያ ሚኒስቴር ህግና አሰራር ውጪ በመቅረቡ መላውን የሀገሪቱ ህዝብና መንግስትን ይቅርታ ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ለመግደል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ቀጠሮ ተጠየቀ

ህንድ

• ህንድ ውስጥ 161 ተሳፋሪቾች የጫነ አንድ አውሮፕላን ለመብረር ከምድር በሚነሳበት ወቅት ከአየር መንገዱን ግድግዳ ጋር ተጋጨ።

ወደ ዱባይ ይበር የነበረው አውሮፕላን ከባድ ጉዳት ባይደርስበትም የህንዷ ከተማ ሙምባይ ውስጥ እንዲያርፍ ተደርጓል።

ጃማይካ

• ጃማይካዊው ዩዚያን ቦልት ለአውስትራሊያው ሴንትራል ኮስት የእግር ኳስ ክለብ ሁለት ግቦችን አስቆጠረ።

የስምነት ጊዜ የኦሎምፒክ አሸናፊው ሩጫ ካቆመ በኋላ ፊቱን ወደ እግር ኳስ በመመለስ የአውስትራሊያውን ክለብ ተቀላቅሎ ነበር።

አሜሪካ

• ባለፈው ዓመት በሞሪታንያ በረሃማ ስፍራ የተገኘው የጨረቃ አካል አሜሪካ ውስጥ ለጨረታ ቀረበ።

5.5 ኪሎ የሚመዝነው የጨረቃ አካል እስከ 500 ሺ ዶላር ድረስ ሊሸጥ እንደሚችል ተገልጿል።

የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ

• የዘጠኝ ዓመቷ አሜሪካዊት ፓይተን ሰመንስ አዕምሮዋ መስራት ስላቆመ ከማሽን እርዳታ ወጥታ ህይወቷ እንዲያልፍ የቴክሳስ ፍርድ ቤት ወሰነ።

ባለፈው ወር ቤተሰቦቿ ወደ ፍርደ ቤት ሄደው በማሽን ታግዛ እንድትቆይ ያስፈቀዱ ሲሆን፤ ጥያቄው ታዳጊዋን ሊያዘልቃት የሚችለው እስከፊታችን ሰኞ ብቻ ነው።

• አሜሪካዊቷ ሙሽራ እጮኛዋ መቃብር ላይ ድል ባለ ሠርግ ተሞሸረች። እጮኛዋ በድንገተና አደጋ የሞተው ቀለበት አድርጎላት፤ ቬሎ ተከራይተው እንዲሁም የሠርጉን ቀን ከቆረጡ በኋላ ነው።

ዩጋንዳ

• ዩጋንዳ ምስራቃዊ ክፍል በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት መንሸራተት ከ30 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።

በአካባቢው የሚገኝ ወንዝ ሞልቶ በመፍሰሱ ከፍተኛ የጭቃ ክምችት በመፈጠሩ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል።

ሜክሲኮ

• በሜክሲኮ የሚገኝ አንድ ሰው በቤቱ ጓሮ ደብቋቸው የነበሩ ሶስት አንበሶችን ለመንግስት አላስረክብም አለ።

ጉዳዩ ከፖሊስ የደረሰው በአንበሶቹ ጩሀት ተረበሽን ያሉ ጎረቤቶች ቅሬታቸውን በማሰማታቸው ነው።

ሙሽሪት እጮኛዋ መቃብር ላይ ድል ባለ ሠርግ ተሞሸረች

ናይጄሪያ

• በናይጄሪያ መንግስት የሚደገፍ የታጣቂዎች ቡድን በቦኮሃራም ተይዘው የነበሩ 833 ህጻናት ወታደሮች ማስለቀቁ ተገለጸ።

ዩኒሴፍ እንደገለጸው ከታዳጊዎቹ መካከል የ 11 ዓመት ህጻናትም ጭምር ነበሩበት።

ኢንዶኔዢያ

• ኢንዶኔዢያ ውስጥ ኢንስታግራምን በመጠቀም ህጻናትን ሲሸጡ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ተጠርጣሪዎቹ የነፍሰ ጡር እናቶችን ፎቶ እንዲሁም የህክምና ማስረጃዎችን በመጠቀም ደንበኞችን ያሳምኑ እንደነበረ ፖሊስ ገልጿል።