የጀርመኗ መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ሥልጣን እንደሚለቁ አሳወቁ

የፎቶው ባለመብት, AFP
የጀመርኗ መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከሁለት ዓመታት በኋላ ሥልጣን እንደሚለቁ አሳወቁ።
ከምርጫ ጋር በተያያዙ አለመግባባቶች ነው መራሂተ-መንግሥት ሜርክል ሥልጣን እርም ልል ነው ሲሉ ያወጁት።
በጀርመኗ በርሊን ከተማ ለተሰበሰቡ ጋዜጠኞች ድምፃቸውን የሰጡት ሜርክል «የሥልጣን ዘመኔ ከተጠናቀቀ በኋላ ፖለቲካ የሚባል ነገር በቃኝ እላለሁ» ሲሉ ተደምጠዋል።
ሲዲዩ የተሰኘው ፓርቲያቸውን ወክለው ማንኛውም ዓይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይም እንደማይሳተፉ አሳውቀዋል።
በጀርመን ባለፈው በተካሄደው ምርጫ የተሳተፉ ፓርቲዎች በቂ ድምፅ ባለማምጣታቸው ምክንያት ተባብረው መሥራት ግድ ሆኖባቸዋል።
የገዥው ጥምር ፓርቲ እህት ድርጅቶችም ድል እየቀናቸው አይደመስልም።
ግራ ዘመሞቹ ግሪንስ እና ቀኝ ዘመሙ ኤኤፍዲ ፓርቲ 'ስደተኞችን ለአፈር' የሚል አቋም በመያዛቸው ምክንያት ከሕዝቡ ድጋፍ እያገኙ ነው ተብሏል።
«ለማንኛውም ደካማ ተግባር» ኃላፊነት እውስዳለሁ ብለዋል መራሂተ-መንግሥት ኤንጌላ ሜርክል።
«እንደሃገሪቱ መሪና እንደ ፓርቲዬ አለቃ፤ ማንኛውም ዓይነት ጥፋትም ሆነ ድል የእኔ እጅ አለበት ብዬ ስለማስብ ኃላፊነት ከመወሰድ ወደኋላ አልልም።»
በእርሳቸው ምትክ የሚሾም/የምትሾም ግለሰብ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ምርጫ እስከተከናወነ ድረስ በጀ ብለው እንደሚቀበሉም ጠቁመዋል።
የገዥው ፓርቲ ፀኃፊ የሆኑት አነግሬት ክራምፕ-ካረንባወር ትክክለኛዋ ምትክ እንደሆኑ ከአሁኑ በመነገር ላይ ይገኛል።
የኤንጌላ ሜርክልን ለስደተኞች ክፍት በር የተሰኘ ፖሊሲን በፅኑ የሚቃወሙት የጤና ሚኒስትሩ ጄንስ ስፓህን ሌላኛው ተቀናቃኝ እጩ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።