ኢትዮጵያዊቷ የኒውዮርክ ነዋሪ የኤል ቻፖን የፍርድ ሂደት ለመዳኘት ተመረጠች

ዮዋኪን ጉዝማን "ኤል ቻፖ" በኒው ዮርክ ከፍተኛ ትበቃ በሚደረግለት እስር ቤት የሚገኝ ሲሆን 11 ክሶች ይጠብቁታል Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ዮዋኪን ጉዝማን "ኤል ቻፖ" በኒው ዮርክ ከፍተኛ ትበቃ በሚደረግለት እስር ቤት የሚገኝ ሲሆን 11 ክሶች ይጠብቁታል

ረቡዕ ዕለት 12 የኒውዮርክ ከተማ ነዋሪዎች የሜክሲኮ ዜጋ የሆነው የአደንዛዥ ዕፅ ነጋዴና ከበርቴ የኤል ቻፖ ጉዝማን ጉዳይን ለመዳኘት ተመርጠው ተሾመዋል። ከመካከላቸውም አንዲት ኢትዮጵያዊ እንደምትገኝ ሮይተርስ ዘግቧል።

በኤል ቻፖ እጣ ፈንታ ላይ ለመወሰን ከተመረጡት 12 ሰዎች መካከል ሰባቱ ሴቶች ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ ወንዶች ናቸው። ጉዳይን ከሚመለከቱ መካከል ሦስቱ በስደት ወደ አሜሪካ የገቡ ናቸው ተብሏል።

ሁሉም በዳኝነቱ የሚሳተፉ ሰዎች ስለ ኤል ቻፖ ሰምተው የሚያውቁ ሲሆን ገለልተኛ ሆኖ ፍርድ ለመስጠትም ቃል ገብተዋል። ኢትዮጵያዊቷ ግን ስለእርሱ "አንዳችም የማወቀው ነገር የለም" ማለቷ ተዘግቧል።

«ያለቋንቋው ሳያስተምር ያደገ ሃገር እኔ አላውቅም» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ

ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል?

ከጉዝማን ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት ኤድዋርዶ ባላሬዞ "በተመረጡት ዳኞቹ ደስተኞች ነን" ብለዋል። አሁን የተሰየሙት ዳኞች ሥራቸውን ማጠናቀቅ ባይችሉ ስድስት ተጠባባቂዎች ተዘጋጅተዋል።

በፍርድ ሂደቱ የሚሳተፉት ሰዎች ማንነት ይፋ የማይገለፅ ሲሆን ወደ ፍርድ ቤቱ ሲገቡም ሆነ ሲወጡም በታጠቁ የፌደራል ፖሊሶች ይታጀባሉ።

አቃቢያነ ህጎቹ የዳኞቹ ደህንነት በሚገባ መጠበቅ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያስረዱ ጉዝማን ምስክሮችን በማስፈራራት ሲከፋም እንዲገደሉ በማዘዝ ስለሚታወቅ ነው፤ ያሉ ሲሆን ጠበቆቹ ግን መሰረተ ቢስ ሲሉ አጣጥለውታል።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
"ከህገ መንግሥት ቀረጻ ጀምሮ ተሳታፊ ነበርኩኝ" - መዓዛ አሸናፊ

በርካታ ዳኞች ለደህንነታቸው በመስጋት በኤል ቻፖ የፍርድ ሂደት ውስጥ አንሳተፍም ማለታቸው ታውቋል።

አራት ወር ሊፈጅ ይችላል የተባለው የፍርድ ሂደት በሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ የተከሳሽ ጠበቆች በሚያቀርቡት አቤቱታ ይጀመራል ተብሏል።

የ61 ዓመቱ ኤል ቻፖ ሜክሲኮ ውስጥ የራሱን የዕፅ ቡድን የሚመራ ሲሆን በዓለም ላይ ኃያል የሆነ የዕፅ አከፋፋይ መረቡን እንደዘረጋ ይነገርለታል።

ጉዝማን ለአሜሪካ ተላልፎ የተሰጠው በ2017 ሲሆን ከሜክሲኮ እስር ቤቶች ሁለት ጊዜ ያህል አምልጦ ተይዟል።

የጉዝማን ጠበቆች ደንበኛቸው በዕፅ ማዘዋወሩ ውስጥ ሚናው ዝቅተኛ እንደነበረው ለማስረዳት መዘጋጀታቸው ተሰምቷል።

የአሜሪካ አቃቤያነ ህጎች በጉዝማን መሪነት ወደ አሜሪካ ሄሮይን፣ ኮኬይን፣ ማሪዋና እና ሌሎች ዕጾችን ያስገባ እንደነበር ገልፀዋል።

ሜክሲኮዋዊው ኤል ቻፖ ጉዝማን አሜሪካ ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ በማዘዋወር የተከሰሰ ሲሆን የፍርድ ሂደቱ በሚቀጥለው ሳምንት ይጀምራል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ