አሜሪካ ለህገ ወጥ ስደተኞች ጥገኝነት መስጠት የሚከለክል ህግ ልታፀድቀቅ ነው

የአሜሪካ ወታደሮች በሜክሲኮ ድንበር አካባቢ Image copyright AFP/Getty

በአሜሪካ አዲስ በሚፀድቀው ህግ መሰረት በሜክሲኮ ድንበር በኩል የሚገቡ ህገወጥ ስደተኞች ጥገኝነት ማግኘት አይችሉም ሲሉ ባለስልጣናት አስታወቁ።

ማንኛውም ግለሰብ በሜክሲኮ ድንበር በሕገወጥ መልኩ የሚገባ ከሆነ ጥገኝነት ቢጠይቅም ማግኘት አይችልም። ህጉ ተግባራዊ የሚሆነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሲፈርሙበት እንደሆነ ተገልጿል።

እንደ ፍትህና አገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር መስሪያ ቤት ባለስልጣናት መግለጫ ከሆነ ሕጉ ጥገኝነት ፈላጊዎች የፕሬዝዳንቱ ክልከላዎችን እንዳይተላለፉ ያደርጋል።

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው ማዕቀብ ተግባራዊ ሊደረግ ነው

ትራምፕ ጠቅላይ አቃቢ ሕጉን አባረሩ

የዲሞክራቶች ድል ለትራምፕ ድንጋጤ

በመግለጫው ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚከለክሉት "የሐገር ጥቅምን" ለማስከበር ነው ተብሎ ተገልጿል።

በቅርቡ በተካሄደው የአካባቢና የምክር ቤት ምርጫ ዘመቻ የስደተኞች ጉዳይ ዋነኛ ማጠንጠኛ ነበር።

ከማዕከላዊ አሜሪካ በሰሜናዊ ሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ ለመግባት እየገሰገሱ የነበሩ ስደተኞችን በተመለከተ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህ "ወረራ" ነው በማለት መግለፃቸው ይታወሳል።

በአሜሪካ አንድ ሰው ጥገኝነት ለመጠየቅ በሚኖርበት ሀገር ለደህንነቱ አደጋ የሆነ ነገር ሊፈጥርና እርሱን ሸሽቶ የመጣ መሆን አለበት።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ