የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ41 ዓመታት በኋላ ወደ ሶማሊያ በረራ ጀመረ

ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ ሰንደቅ አላማ የተሰራ ኬክ
አጭር የምስል መግለጫ ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ ሰንደቅ አላማ የተሰራ ኬክ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ41 ዓመታት በኋላ ወደ ሶማሊያ በረራ አድርጎ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ አረፈ።

በቦይንግ 737 የተደረገው በረራ የተመራው በሴት አውሮፕላን አብራሪ ሲሆን፤ 50 ሰዎችን አሳፍሮ ነበር።

በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ ድንበር ላይ የጅምላ መቃብር ተገኘ

አሜሪካ ለህገ ወጥ ስደተኞች ጥገኝነት መስጠት ልትከለክል ነው

አውሮፕላኑ ሞቃዲሾ የደረሰው ከአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ሁለት ሰአት ገደማ ከበረረ በኋላ ነበር። ከተሳፋሪዎቹ መካከል በኢትዮጵያ የሶማሊያ ኤምባሲ ፈርስት ካውንስለር አቶ አብዱላሂ መሀመድ ዋርፋ ይገኙበታል።

አቶ አብዱላሂ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በረራው መጀመሩ የሁለቱን ሀገሮች የንግድ ግንኙነት ያጠናክራል።

አውሮፕላኑ ከአዲስ አበባ ሲነሳ፣ በበረራው እኩሌታ እንዲሁም ሞቃዲሾ ካረፈ በኋላ ልዩ ልዩ መሰናዶዎች ተካሂደዋል።

ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት?

"የቅማንትን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ፅንፈኞች ከሌሎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው" ጄኔራል አሳምነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሶማሊያ በረራ ማድረግ ያቋረጠው እንደ አውሮፓውያኑ በ1970ዎቹ በሁለቱ ሀገሮች የድንበር ግጭት ከተከሰተ በኋላ ነበር።

በአሁን ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሶማሊያው ፕሬዘዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆና ከኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ይገኛሉ።

Image copyright OMAR FARUK OSMAN
አጭር የምስል መግለጫ የኬክ ቆረጣ ስነ ስርዓት ተካሂዷል
Image copyright Omar Faruk Osman
አጭር የምስል መግለጫ ጋዜጠኞች ተገኝተው ነበር
Image copyright Omar Faruk Osman
አጭር የምስል መግለጫ አቶ አብዱላሂ መሀመድ ዋርፋ
አጭር የምስል መግለጫ አውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ
Image copyright Omar Faruk Osman
አጭር የምስል መግለጫ የሶማሊያ ባህላዊ ሙዚቃ ቀርቧል

ተያያዥ ርዕሶች