የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ተዋሃዱ

የኦዲግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ እና የኦዴግ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ
አጭር የምስል መግለጫ የኦዲግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ እና የኦዴግ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ-ኦዴፓ እና በሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር-ኦዴግ ለመዋሃድ የመግባቢያ ሰነድ ላይ ዛሬ ከሰዓት ተፈራረሙ።

በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል የፖለቲካ መርህ ልዩነት አለመኖሩ እና በህዝብ ዘንድ ሁለቱ ፓርቲዎች እንዲዋሃዱ ፍላጎት መኖሩ ሁለቱ ፓርቲዎች እንዲዋሃዱ ምክንያት ሆኗል ተብሏል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት እና የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ፤ ''በአንድ አዕምሮ እና ልብ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰናል። ኦዴፓ በወጣቶች የተሞላ ፓርቲ ነው። ከኦዴግ ጋር ስንዋሃድ ጠንካራ ተቋም ይወጣናል'' ብለዋል። የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር አመራሮች ወደ ሃገር ከመምጣታቸው በፊት ''ሲረዱን'' ነበር ያሉት ፕሬዚዳንት ለማ፤ አብረን ለመስራት እድሉን ስላገኘን ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል ብለዋል።

''ለአንድ ኦሮሞ ህዝብ ከ10 በላይ ሆነን ከምንታገል፤ ከእኛ ጋር አንድ አይነት ዓላማ እና ሰልት የሚከተሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን መጥተው ቢቀላቀሉን አሁንም ለመቀበል ዝግጁ ነን። ይህም ለኦሮሚያ ብቻ ሳይሆን ለሃገርም ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው።'' ብለዋል።

". . . ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል" ጠ/ሚ ዐብይ

"ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም

ምርጫ ፡ የተቃዋሚዎችና የመንግሥት ወግ?

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታ በበኩላቸው ''የመበታተን ባህል ወደ ችግር እና ድህነት ነው የሚወስደን'' ብለዋል። አቶ ሌንጮ ጨምረው ''ዛሬ ላይ የፓርቲዎች ውህደት ብቻ ሳይሆን የህዝብ አንድነት ጭምር ያስፈልገናል፤ የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሳይሆን እንደዛሬ ነው ማሰብ ያለብን'' ሲሉ ተናግረዋል።

የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ በህዝቡ ዘንድ ፓርቲዎቹ እንዲዋሃዱ ያለው ፍላጎት እንዲሁም በኦዴፓ እና ኦዴግ መካከል የፖለቲካ መርህ ልዩነት አለመኖር ፓርቲዎቹ እንዲዋሃዱ ምክንያት ሆኖዋል ብለዋል።

ከፓርቲዎቹ ውህደት በፊት ረዘም ያለ ውይይት መካሄዱን ያስታወሱት አቶ አዲሱ፤ ወደፊትም አንድ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ የፓርቲ መጠሪያ ስያሜ፣ አርማ እና በመሰል ሌሎች ጉዳዮች ላይ ይሰራል ብለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ