ቶጎዋዊያን ተመራማሪዎች የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻን ወደ ሮቦቶች ቀይረዋል

በሸረሪት ቅርፅ የተሰራ ሮቦት
አጭር የምስል መግለጫ ከተጣለ ማተሚያ ማሽን በሸረሪት ቅርፅ የተሰራ ሮቦት

ቶጎ በየዓመቱ ወደ ሀገሯ ከምታስመጣቸው 500 ሺህ ሰልባጅ ኤልክትሮኒክሶች መካከል አንዳንዶቹ ለጤና ጠንቅ ቢሆኑም እንኳ የሀገሪቱን ወጣት ተመራማሪዎችን ግን ለአዳዲስ ፈጠራ አነሳስቷቸዋል።

ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በመንግሥት ወይም በግለሰቦች ጥቅም ላይ ውለው ከተወገዱ በኋላ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ቆሻሻ ይሆናሉ።

የ29 ዓመቱ ቶጓዊ ሀገሩ የምታስገባቸው የኤሌክትሮኒክስ ውድቅዳቂዎችን በመሸጥ ይጠቀማል።

አነስተኛ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ የሚያክል ስፍራ ላይ ያገለገሉ ቴሌቪዥኖችና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ተከምረው ይታያሉ።

ከእነዚህ ውድቅዳቂና ያገለገሉ እቃዎች በቶጎ የመጀመሪያውን ስሪ ዲ ማተሚያ እንደሰራ የሚናገረው ጊንኮ አፋቴ ያገለገሉ እቃዎችን መልሶ ጥቅም ላይ ስለማዋል በርካታ ነገሮች እንደተማረ ይናገራል።

የእርሱ ፈጠራ እውቅና አግኝቶ በ2015 በባርሴሎና የቴክኖሎጂ ምርቶች ጉባኤ ላይ ቅድሚያ አግኝቷል።

ከዚህ በፊት የተጣሉ እቃዎችን እየሰበሰቡ የተለያዩ ነገሮች ከሚሰሩ ወዳጆቹ ጋር በህብረት ይሰራ የነበረው የ39 ዓመቱ የፈጠራ ባለሙያ ዛሩሬ የራሱን መስሪያ ቦታ ከፍቷል።

"የቶጎ ጎዳናዎች ባገለገሉ እቃዎችና በበሰበሱ የኮምፒውተር አካላት ተሞልተው ነበር። ዛሬ ይህ ነገር አይታይም። አሁን የቆሻሻ ክምር ሳይሆን የወርቅ ጉድጓድ ነው የሚታየኝ" ይላል ለፈጠራ የሚያነሳሳውን የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ ሲያስታውስ።

በዓለም ላይ 41 የአውሮፓ ሀገራት ብቻ ናቸው ስለሚያስወግዷቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መረጃ የሚይዙት።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
ከ1 ሰው 140 ፈጠራ ?

ረሃብ የቀሰቀሰው ፈጠራ

ያገለገሉ የሞባይል ቀፎዎች፣ ላፕቶፖች፣ ቴሌቪዥኖች፣ ጄኔሬተሮች፣ በእቃ መጫኛ መኪናዎች ተጭነው ከሎሜ ወደብ ይመጣሉ።

መኪኖቹ እቃዎቹን የሚያራግፉት ከወደቡ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኝ የገበያ ስፍራ ነው። ያኔ ሰልባጅ እቃዎችን ለመግዛት የሚረባረቡ ሰዎች ቁጥር አይን አይቶ አይሰፍረውም።

ሸማቾች ለቴክኖሎጂ ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ ሰልባጅ እቃዎችን በድርድር ዋጋ መግዛት ጀምረዋል።

ያገለገሉ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፍላጎት መኖር ብቻ ሳይሆን ባደጉ ሀገራት ያገለገሉ እቃዎችን መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ነገር በበቂ ሁኔታባለመኖሩ ቶጎን መጣያ አድርጓታል።

እኤአ በ2016 በዓለማችን 44 ሚሊየን ቶን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ቆሻሻ እንደተሰበሰበ ተገልጾ ነበር።

ከዚህ ውስጥ 20 በመቶው ብቻ ተመልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል።

የታኘከ ማስቲካ ዳግም ነብስ ሲዘራ

ዘመናዊውን የመፀዳጃ መቀመጫ የፈጠረው ሰዓት ሠሪ

በ2021 ይህ ወደ 52 ሚሊየን ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ