በህንድ ግማሽ ብርጭቆ ውሃ እየተሸጠ ነው የሚልና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

ኢትዮጵያ

• የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በፈረንጆቹ 2018 ዓመተ ምህረት የፎርብስ መፅሄት 100 ተፅእኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ።

የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል፣ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ፣ ኦፕራ ዊንፍሬይና ሌሎች ምሁራን እነዲሁም ስፖርተኞች በዝርዝሩ ተካተዋል።

• የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፤ አብዴፓ በሰመራ እያካሄደው ባለው 7ኛው መደበኛ ጉባኤ 72 የድርጅቱ አባላትን አሰናበተ።

የአብዴፓ ሊቀመንበርና የክልሉ ርእሰ መስተዳደር የነበሩት ሀጂ ስዩም አወል ደግሞ ከተሰናባቾቹ መካከል መሆናቸው ተገልጿል።

የኦሮሚያ ተቃውሞዎች ምን ይጠቁማሉ?

እንግሊዝ አጭበርባሪ ባለሀብቶችን ቪዛ ልትከለክል ነው

ደቡብ አፍሪካ

• ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በየሰአቱ የሚከሰት የመብራት መጥፋት ነዋሪዎችን ከማስመረር አልፎ ኢኮኖሚውን እየጎዳ ነው ተባለ።

ኤስኮም የተባለው የኤሌክትሪክ አቅራቢ ደግሞ ድርጅቱ መብራት የሚያጠፋው የሃይል ማስተላለፊያ ማዕከሉ ካለበት ጫና አንጻር እንዳይፈነዳ በማሰብ ነው ብሏል።

ቡሩንዲ

• ቡሩንዲ በሃገሪቱ የሚገኘውን የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብት ካውንስል ቢሮን በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ልትዘጋ ነው።

ሃገሪቱ ከዚህ በፊት ከአለማቀፉ ፍርድ ቤትና ከምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ጉባኤ እራሷን አግልላለች።

ላይቤሪያ

• ላይቤሪያ ውስጥ 60 በመቶ የሚሆነው የሃገሪቱ የኤልክትሪክ አቅርቦት በግለሰቦችና ድርጅቶች እንደሚሰረቅ ተገለጸ።

በዚህም ሳቢያ ከሃገሪቱ ዜጎች 12 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ኤሌክትሪክ የሚያገኙ ሲሆን፤ ከ945 ሚሊየን ብር በላይ ደግሞ ይከስራል።

ማሌዢያ

• የማሌዢያ ባለስልጣናት በህገወጥ መንገድ የተያዘ ከ234 ሚሊዯን ብር በላይ የሚያወጣ ፓንጎሊን የተባለ እንስሳ ቅርፊት አቃጠለች።

ለመድሃኒትነት የሚውሉት ቅርፊቶቹ ከአፍሪካ የመጡ ሲሆን፤ 3000 የሚደርሱ ፓንጎሊኖች ሳይገደሉ እንዳልቀረ ተገምቷል።

አሜሪካ

• በአሜሪካዋ ቴኔሲ ግዛት ማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኝ ታራሚ በኤሌክትሪክ ንዝረት እንዲገደል ጠየቀ።

ታራሚው እንደገለጸው ከሆነ ከውሳኔ የደረሰው በመርዝ የመሞት ሌላኛው አማራጭ ህመም ሊኖረውና ሊያሰቃየው ስለሚችል ነው።

ኒካራጉዋን

• ኒካራጉዋን ውስጥ የምዕመናንን ኑዛዜ ሲቀበል የነበረ ቄስ የአሲድ ጥቃት ደረሰበት።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አንዲት ሴት በአካባቢው በነበሩ ምዕመናን በቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን፤ መነሻው ምን እንደሆነ ግን አልታወቀም ተብሏል።

የኦሮሞ ፓርቲዎች የጋራ ፎረም ለማቋቋም ከስምምነት ላይ ደረሱ

ፑቲን፡ አሜሪካ ስምምነቱን ጥላ ከወጣች ሩሲያ ሚሳዬል ትገነባለች

ፊንላንድ

• ጉግል ሰው አልባ አውሮፕላኖች በመጠቀም የተለያዩ እቃዎችን ቤት ለቤት የማድረስ የሙከራ ስራውን በፊንላንድ ጀመረ።

ሰው አልባ አውሮፕላኖቹ እስከ 1.5 ኪሎ መሸከም የሚችሉ ሲሆን፤ ትዕዛዝ በተቀበሉ በደቂቃዎች ውስጥ ከበር ደጃፍ ላይ ይደርሳሉ ተብሏል።

የመን

• የመን ውስጥ የእርስ በእርስ ጦርነቱ ከተከሰተ ከሁለት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለቱም ተዋጊ ቡድኖች ለመደራደር ተስማሙ።

የድርድሩ አስተባባሪ የተባበሩት መንግስታት ውይይቱ ስዊድን ውስጥ እንደሚካሄድ አስታውቋል።

ሆላንድ

• ሆላንድ ውስጥ የ16ኛ ዓመት የልደት በአሏን ለማክበር ጓደኞቿን ብቻ የጠየራችው ታዳጊ ያልተጠበቁ 4000 እንግዶች በመምጣታቸው ፖሊስ እነዲጠራ ግድ ሆነ።

በፌስቡክ የተለቀቀውን መልዕክት የሰሙ ወጣቶች አንመለስም በማለታቸው በፖሊስ እንዲበተኑ ግድ ሆኗል።

ህንድ

• በምዕራባዊ ህንድ ፑን ግዛት የሚገኙ 4000 ምግብ ቤቶች ግማሽ ብርጭቆ ውሃ ማቅረብ እነደጀመሩ ተገለጸ።

ምክንያቱ ደግሞ በመላ ሃገሪቱ 600 ሚሊዮን ሰዎችን ያጠቃው የውሃ እጥረት ነው።