12 የጤና ባለሙያዎች በኢቦላ ሞቱ የሚሉና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

Image copyright Reuters

ኢትዮጵያ

• ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች ጋር ቆይታ አደረጉ።

ታዳጊዎች ኢትዮጵያዊነትን የሚያደምቁ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚሰሩና የሚመሩ በመሆናቸው ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል ብለዋል ጠቅላዩ።

ቤኒን

• በደቡብ ምዕራባዊ ቤኒን ነዋሪዎችን ያስቸገረ አንበሳ የሚያፈላልግ ከፖሊስ፣ አዳኞችና የደን ባለሙያዎች የተውጣጣ ቡድን ተቋቋመ።

አንበሳው የአካባቢው ነዋሪዎችን ላለፉት ሶስት ሳምንታት ሲያስጨንቅ ነበር ተብሏል።

የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ

አፍሪካ የተሰጣትን ጨለምተኛ እይታ ለመቀየር ያለመው አዲስ ፎቶ ፌስት

ዛምቢያ

• የዛምቢያው የህገ መንግስት ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉ ለሶስተኛ ጊዜ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እንዲሳተፉ ፈቀደላቸው።

ፕሬዝዳንቱ የቀድሞውን መሪ ተክተው በመምጣታቸው ምክንያት ህገመንግስቱን አይጥሱም ብሏል ፍርድ ቤቱ።

ዴሞክራቲክ ኮንጎ

• በዴሞክራቲክ ኮንጎ በኢቦላ ተይዘው ከነበሩት 44 የጤና ባለሙያዎች 12ቱ ህይወታቸው ማለፉን የሃገሪቱ የጤና ሚኒስትር ገለጸ።

እስካሁን በበሽታው ምክንያት ባጠቃላይ 273 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

ሴኔጋል

• ሴኔጋል በመላው ዓለም የሚገኙ የጥቁር ህዝቦችን ስልጣኔ የሚያሳይ በ34 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባ ሙዚየም አስመረቀች።

ሙዚየሙ ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ቅርሶችን ከመያዙ በተጨማሪ የኩባና ሄይቲ ቅርሶችንም አካቷል።

ከስም ፊት የሚቀመጡ መለያዎና አንድምታቸው

ለየት ያለ ደም ላላት ህፃን "የለጋሽ ያለህ" እየተባለ ነው

• አፍሪካ በመኪና አደጋ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ የሆነባት አህጉር እንደሆነች የአለም ጤና ድርጅት ገለጸ።

በሪፖርቱ መሰረት ከእያንዳንዱ 100 ሺ ሰው 27 የሚሆኑት በመኪና አደጋ ይሞታሉ።

ህንድ

• አንድ ህንዳዊ የሂንዱ ሃይማኖት ቤተ አምልኮን በተመለከተ በትዊተር ገጹ የቀለደው ቀልድ ለእስር ዳርጎታል።

ሰውዬው ከአንድ ወር በላይ በእስር የቆየ ሲሆን፤ ከስህተቱ ታርሟል በማለት ፍርድ ቤቱ አሰናብቶታል።

አፍጋኒስታን

• ሊትል ሜሲ የሚል ስያሜ ያገኘው አፍጋኒስታናዊው ህጻን ከታሊባን በደረሰው ማስፈራሪያ ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ ከመኖሪያ መንደሩ ተሰደደ።

ህጻኑ በ2016 የዓለምን ቀልብ መግዛት ችሎ የነበረ ሲሆን፤ ታዋቂው እግር ኳሰኛ ሊዮኔል ሜሲ ቲሸርቱን ልኮለትም ነበር።

ቼልሲ ከሲቲ፡ የላውሮ የፕሪሚየር ሊግ ግምቶች

አሜሪካ

• አሜሪካ ውስጥ በካንሰር ህመም እየተሰቃየች ያለች የሁለት ዓመት ህፃን ለማዳን የተለየ የደም ዓይነት ከለጋሾች ለማግኘት ዓለም አቀፍ ዘመቻ ተጀመረ።

እስካሁን አንድ ሺህ የሚደርሱ የደም ናሙናዎች ቢቀርቡም፤ ከእሷ ደም ጋር ተዛማጅ ሆነው የተገኙት ሦስቱ ብቻ ሲሆኑ፤ ለህፃኗ 10 ተመሳሳይ ደም ያላቸው ለጋሾችን ማግኘት ያስፈልጋል።

ተያያዥ ርዕሶች