የምርጫ ቦርድን እንደገና ለማቋቋም በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ፓርቲዎች እየመከሩ ነው

የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ከውይይቱ በኋላ በሻይ እረፍት ላይ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን እንደገና ለማቋቋም የተረቀቀ አዋጅ ዛሬ ረቡዕ በአዲስ አበባ ለምክክር ቀርቧል። በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፤ የሕግ እና የፍትህ አማካሪ ጉባዔ ጽህፈት ቤት በተሰናዳው የምክክር መድረክ ላይ በርካታ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና ተወካዮች ተገኝተዋል።

አሁን ባለው የኢትዮጵያ የሕግ መዋቅር መሰረት ምርጫን የሚመለከቱ ሦስት ሕጎች ሲኖሩ፤ የምርጫ ሕጉ አንዱ ነው። ሌሎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ሕግ እና የምርጫ ሥነ ምግባር ሕግ ናቸው።

ብርቱካን ሚደቅሳ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንደሚሾሙ ይጠበቃል

ዲሞክራሲያዊ፣ ነፃ እና ፍትሃዊ የሆነ ምርጫን ከማካሄድ አንፃር እነዚህ ሕግጋት ያሉባቸው ክፍተቶች በልዩ ልዩ መስፈርቶች መገምገማቸውን የተናገሩት በጉባዔው የዲሞክራሲ ተቋማት ጥናት ቡድን አባል የሆኑት እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሕግን የሚያስተምሩት ዶክተር ሲሳይ አለማው ናቸው።

አሁን ለምክክር የቀረበው ግን የምርጫ ቦርዱን ብቻ የሚመለከተውና በአዋጅ ቁጥር 532/99 የተካተተው መሆኑን ዶክተር ሲሳይ ገልፀዋል።

"ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት በመንግሥት በኩል ምርጫ ቦርድን እንደገና ገለልተኛ እና ተዓማኒነት ያለው አድርጎ እንዲሁም ለሥራ አፈፃፀም ቅልጥፍና ባለው መልኩ ለማቋቋም ባለው ፍላጎት እና ጥያቄ መሠረት ነው" ብለዋል የጥናት ቡድን አባሉ።

"ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ረቂቅ አዋጁ የቦርዱ አቋም በአጠቃላይ ምን መምስል አለበት፣ አባላቱ እንዴት ሊመለመሉ እና ሊነሱ ይችላሉ፣ ስልጣናቸውስ ምን ይመስላል የሚለውን በዝርዝር የሚያስቀምጥ ይሆናል።

ይኖራሉ ተብለው ከሚጠበቁ ለውጦች መካከል አንዱ በትርፍ ሰዓት ከሚሰሩ አባላት ወደ ሙሉ ሰዓት ማሸጋገር እንደሆነ ዶክተር ሲሳይ ተናግረዋል።

በረቂቁ ውስጥ እንደተካተተው ከሆነ የቦርዱ ሠራተኞች የሙሉ ሰዓት ሰራተኛ ሆነው ቁጥራቸው ሊያንስ ይችላል።

ምርጫ ፡ የተቃዋሚዎችና የመንግሥት ወግ?

እነርሱም በቦርዱ ሥራ ውስጥ የተሻለ ተሳትፎ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ያስረዱት ዶክተር ሲሳይ፤ ቦርዱ በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ምርጫዎችን እና ሕዝበ ውሳኔዎችን እንደማስተዳደሩ፣ ከዚያም በዘለለ የሥነ ዜጋ ትምህርት የመስጠት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ ስልጣናት ስላሉት ዝቅ እስካሉ የአስተዳደር አሃዶች የሚደርስ መዋቅር ቢኖረው ተገቢ ይሆናል ተብሎ እንደታሰበ አትተዋል።

ለምክክር የቀረበው ረቂቅ ሕግ የምርጫ ቦርድ በጀቱን ከማስተዳደር አንስቶ የምርጫ አስፈፃሚዎችን እስከ መቅጠር ድረስ ሙሉ ስልጣን እንዲኖረው የሚያስችል ነውም ተብሏል።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት እና ትልቅ ስፋትም ያላት አገር እንደመሆኗ ምርጫ ቦርድ "በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ስለሚያሰማራ በቂ ጊዜና በጀት አግኝቶ በነፃነትና በገለልተኛነት መስራት የሚችልበት ማዕቅፍ እንዲኖር ነው ይህ ረቂቅ የቀረበው" ብለዋል ዶክተር ሲሳይ።

የሰልፍ "ሱሰኛው" ስለሺ

ረቂቅ ሕጉ እንደሚለው የህገ መንግሥቱን መሠረተ ነገር በሚያንፀባርቅ ሁኔታ የቦርዱ አባላት የብሄር ተዋፅዖን ግምት ውስጥ በማስገባት እንደሚመረጡም ተገልጿል።

ረቂቅ ሕጉ አንድን ምርጫ ታሳቢ በማድረግ የተሰናዳ ሳይሆን ረዥም ጊዜን አሻግሮ በማየት የተቀረፀ ነው የተባለ ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች በእነዚህ እና በሌሎችም በህጉ በተካተቱ ሃሳቦች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ