የጭንቅላት ቀዶ ጥገና እየተደረገለት ጊታር የተጫወተው ግለሰብ

MUSA MANZINI Image copyright COURTESY OF MUSA MANZINI

ደቡብ አፍሪቃዊው የጃዝ ሙዚቃ ተጫዋች ሙሳ ማንዚኒ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና እየተደረገለት ጊታሩን ሲቃኝ ነበር፤ አሁን ላይ የሚገኝበት ሁኔታም እጅጉን መልካም እንደሆነ ተነግሯል።

ስድስት ሰዓታትን በፈጀው ቀዶ ጥገና ላይ ሙሳ ጊታር እንዲጫወት የሆነው ዶክተሮቹ ቀዶ ጥገናውን ሲያከናውኑ እንዲመቻቸው ነው ተብሏል።

የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ የሆነው ሙሳ የሙዚቃ ተጫዋች በመሆኑ የጭንቅላት ቀዶ ጥገናው የጣቶቹ እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለመየት ያስችል ዘንድ ነው ጊታር እንዲጫወት የተፈቀለደት።

«ሰው ሲበሳጭ ማስታወሻ እይዝ ነበር» አዲስ ዓለማየሁ

ቀዶ ጥገናው በሙያው ጥርሳቸውን በነቀሉ የደቡብ አፍሪቃ የጭንቅላት ቀዶ-ጥገና ስፔሻሊስቶች ነው የተካሄደው።

ሙሳ፤ በግሪጎሪ አቆጣጠር 2006 ነበር ከጭንቅላት ዕጢ ጋር በተያያዘ በሽታ ተጠቅቶ የነበረው፤ ሁኔታው ሲጠናበት ግን ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል መግባት ግድ ሆነበት።

ከቀዶ ጥገና ስፔሻሊስቶቹ አንዱ የሆኑት ዶክተር ኤኒከር እንዲህ ታካሚዎች ንቁ ሆነው ሳለ የሚካሄድ ሕክምና አንዳንዴ ተመራጭ ነው ይላሉ።

ቀዶ ህክምና በአፍሪካ ስጋት መሆኑ ከፍ ብሏል

«ዕጢውን በቀለለ ዘዴ ማስወገድ እንድንችል ያግዘናል፤ አልፎም የትኛው የሰውነት ክፍል እየሠራ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን በግልፅ ማየት እንችላለን።»

ምናልባት ሙሳ በማደንዘዣ እንዲተኛ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ የተወሰነ የሰውነት ክፍሉ 'ፓራላይዝ' ሊሆን ይችል እንደነበር ባለሙያዎቹ ይናገራሉ።

በሙዚቃ ሥራው ሽልማት ማግኘት የቻለው ሙሳ ለተደረገለት የተሳካ ቀዶ ጥገና ዶክተሮቹን ሳያመሰግን አላለፈም።

በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው