ከስካውት አባሎች እስከ ስደተኛ እናትና ልጅ፡ የአፍሪካ ሳምንት በፎቶ
እናት አፍሪካ ሳምንቱን እንዴት አሳለፈች? 'ይናገራል ፎቶ' እንዲሉ እነዚህ ፎቶዎች ሳምንቱን ያስቃኙን ዘንድ መርጠናቸዋል። ያሰባሰብናቸው ከኤኤፍፒ፣ ከኢፕኤ፣ ከሮይተርስና ከጌቲ ኢሜጅስ ነው።
የሪፐብሊክ ጥበቃ ኃይሉ ትርዒት ሲያሳይ
የፎቶው ባለመብት, Ethiopia PM office twitter page
እሁድ ዕለት ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የሪፐብሊክ የጥበቃ ኃይሉ ማንኛውንም ጥቃት ለመከላከልና ለመመከት ያለውን ዝግጁነት ለማሳየት ያቀረበውን ትርዒት ተመልክተዋል።
የደቡብ አፍሪካው አሳ
የፎቶው ባለመብት, EPA
'ስታርፊሽ' የተባለው የአሳ ዝርያ ነው። ፎቶ ያነሳው በደቡብ አፍሪካ የውሀ ውስጥ ስነ ህይወት ጥናት (ማሪን ባዮሎጂ) ተማሪ ኬፕ ታውን ውስጥ ከውሀ በታች ቅኝት ሲያደርግ ነበር።
ኬንያ በፈረንጆች ገና
የፎቶው ባለመብት, Reuters
የዘንድሮው የፈረንጆች ገና ኬንያ- ናይሮቢ ውስጥ ሲከበር፤ ኡሁሩ ፓርክ ውስጥ የሚገኝ የውሀ ትቦ ፈንድቶ የበዐሉ አክባሪዎች በውሀ ተራጭተዋል።
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ስካውቶች
የፎቶው ባለመብት, AFP
በምዕራባዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ታዳጊ የስካውት አባላት ገናን በቤተ አምልኮ ተገኝተው አክብረዋል።
ታዳጊዋ በካሜራ እይታ
የፎቶው ባለመብት, AFP
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ገና ሲከበር ይቺ ታዳጊ በካሜራ እይታ ውስጥ ገብታለች።
የግብጽ ገበያ
የፎቶው ባለመብት, EPA
በግብጽ- ካይሮ ገና እንዲሁም የ2019 መምጣት ሲከበር፤ የ 'ሳንታ ክላውስ' አሻንጉሊቶች ይሸጡ ነበር።
ኳስ በሊቢያ
የፎቶው ባለመብት, Reuters
ሊቢያ-ትሪፖሊ በሚገኝ የእግር ኳስ ማሰልጠኛ ውስጥ ሴት ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ልምምድ ማድረግ ችለዋል።
እናትና ልጅ ስደተኞች በሊቢያ
የፎቶው ባለመብት, AFP
በሊቢያ ጠረፍ የተነሳ ፎቶ ነው። አንዲት እናትና ጨቅላ ልጇ ከ300 ስደተኞች ጋር በሕይወት ከተረፉ በሏላ፤ በሄሊኮፕተር ወደ መጠለያ ተወስደዋል።
በሕይወት የተረፈው ጨቅላ
የፎቶው ባለመብት, AFP
ስደተኛ እናትና ጨቅላ ልጇ ሊቢያ ውስጥ በሕይወት ከተረፉ በኋላ ጨቅላው ማልታ የሚገኝ ሆስፒታል ተወስዷል።