ሳይንቲስቱ በዘረኛ ንግግራቸው ማዕረጋቸውን ተቀሙ

ሳይንቲስቱ ጄምስ ዋትሰን ዘረኛ ንግግር ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው አይደለም Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ሳይንቲስቱ ጄምስ ዋትሰን ዘረኛ ንግግር ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው አይደለም

አሜሪካዊው ሳይንቲስት ዶ/ር ጄምስ ዋትሰን በአንድ የቴሌቭዥን መሰናዶ ላይ ዘረኛ ንግግር ካደረጉ በኋላ ለሥራቸው ዕውቅና የተሰጣቸውን ማዕረግ ተነጥቀዋል።

በዘረ መል ምርምር የሚታወቁት የኖቤል ተሸላሚው ሳይንቲስት፤ የጥቁሮችና ነጮች አይኪው (የማሰላሰል ብቃት እንደማለት) በዘረ መላቸው ይወሰናል የሚል ዘረኛ ንግግር አድርገዋል።

የዘንድሮ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊዎች

'ኮልድ ስፕሪንግ ሀርበር' የተባለው ቤተ ሙከራ፤ የ90 ዓመቱ ሳይንቲስት ያደረጉትን ንግግር በማስረጃ ያልተደገፈና ሀላፊነት የጎደለው ሲል ተችቷል።

ሳይንቲስቱ እንደ አውሮፓውያኑ በ2007 በተመሳሳይ ዘረኛ አስተያየት ሰንዝረው ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል።

«ስጦታ ከመቀበል፤ መስጠት ያዋጣል»

በ1962 የዘረ መል ምርምርን በተመረኮዘ ግኝት ሞሪስ ዊልኪንስ ከተባሉ ተመራማሪ ጋር በጋራ የኖቤል ሽልማት አግኝተዋል።

ዶ/ር ጄምስ ዋትሰን ዘረኛ ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ ከሳይንሱ ማኅበረሰብ አግልሏቸው ነበር። በዚህ የተነሳም በ2014 የወርቅ ሜዳልያቸውን ሸጠዋል።

ሳይንቲስቱ በ2007 ለታይምስ ጋዜጣ "ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መዋቅር የመሰረትነው አፍሪካውያን ከኛ እኩል ያሰላስላሉ የሚል እሳቤ ላይ ተመርኩዘን ነው። ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ግን ከኛ እኩል አያስቡም" ሲሉ ጥቁሮችን የሚያንቋሽሽ አስተያየት ሰጥተዋል።

በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት

ከዚህ ንግግር በኋላ ሳይንቲስቱ ከሚመሩት ቤተ ሙከራና የአስተዳደር ሥራዎች ተነስተዋል። ከዚያም ይቅርታ ጠይቀው የማዕረግ ስማቸውን ይዘው እንዲቆዩ ተፈቅዶላቸው ነበር።

'ኮልድ ስፕሪንግ ሀርበር' ሳይንቲስቱ ከዚህ ቀደም ይቅርታ ቢጠይቁም አመለካከታቸው ባለመለወጡ ማዕረጎቻቸውን ለመቀማት ውሳኔ አስተላልፏል።

'ኮልድ ስፕሪንግ ሀርበር'፤ "ዶ/ር ዋትሰን ያደረጉት ንግግር ክብረ ነክ ነው። በሳይንስ የተደገፈም አይደለም" የሚል መግለጫም አውጥቷዋል።

ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ

ዶ/ር ዋትሰን የተቋሙ ዳይሬክተር ከዛም ፕሬዚዳንት ነበሩ። ቤተ ሙከራው ውስጥ የሚገኝ ትምህርት ቤት በስማቸው ተሰይሟል።

ተያያዥ ርዕሶች