የሱዳን ተቃዋሚዎችን ባለመደገፋቸው ተቃውሞ የገጠማቸው ኢማም

ካርቱም አደባባይ የወጡት ተቃዋሚዎች Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ካርቱም አደባባይ የወጡት ተቃዋሚዎች

ካርቱም የሚገኙ ኢማም የኦማር አል-በሽር ተቃዋሚዎችን ባለመምራታቸው ከመስጅድ ተባረዋል።

ሱዳን ውስጥ ካሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀይማኖታዊ መሪዎች አንዱ የሆኑት ኢማም አብዱል ሀይ ዩሱፍ ከመስጅድ የተባረሩት አማኞች "ተቃውሞውን እየመሩ አይደለም" ሲሉ ከወነጀሏቸው በኋላ ነበር።

በሱዳን የዳቦ ዋጋ በመጨመሩ ተቃወሞ ተቀስቅሷል

ኢማሙ ተከታዮቻቸውን ከጋዛ እና ሶርያ ጋር አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ በመጠየቅ ይታወቃሉ።

በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል፤ መንግሥትን በመደገፍ የሚታወቁትን ኢማም አንድ ግለሰብ ሲቆጣ ይታያል። በእርግጥ የምስሉን ትክክለኛነት ማጣራት አልተቻለም ነበር።

"ጫትን ማገድ ፈፅሞ የሚቻል አይደለም" ዶ/ር ዘሪሁን መሃመድ

ትራምፕ ቱርክን አስጠነቀቁ

ባለፈው አርብ ዕለት ከስግደት በኋላ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ "አገዛዙ መውደቅ አለበት" የሚል ተቃውሞ ተስተጋብቷል። ፖሊሶች ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተጠቅመዋል።

ሮይተርስ እንደዘገበው፤ የአርቡ ተቃውሞ ከሌላው ጊዜ የላቀ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎች የተሰባበሱበት ነበር። ተቃዋሚዎቹን የጸጥታ ሀይሎች የበተኗቸው ሲሆን፤ የተጎዳ ሰው ስለመኖሩ የተዘገበ ነገር የለም።

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ባለፉት ሦስት ሳምንታት 20 ሰዎች መገደላችው ተዘግቧል

የሱዳን ተቃውሞ የተቀጣጠለው መንግሥት በነዳጅና በዳቦ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉን ካስታወቀ በኋላ ሲሆን፤ ባለፉት ሦስት ሳምንታት 22 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።

የዋጋ ንረት የበርካታ ሱዳናውያን ራስ ምታት ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል። ደቡብ ሱዳን አብላጫውን የነዳጅ ሀብት ይዛ መገንጠሏም ሀገሪቱ ከገጠሟት መሰናክሎች አንዱ ነው።

ሳይንቲስቱ በዘረኛ ንግግራቸው ማዕረጋቸውን ተቀሙ

ከ20 ዓመታት በላይ የዘለቀው የአሜሪካ ማዕቀብም ሌላው ተግዳሮት ነበር።

ሦስት አሰርታት ያስቆጠረው የአል-በሽር አገዛዝ በሰብአዊ መብት ጥሰት ይተቻል።

እንደ አውሮፓውያኑ በ2009 እና በ2010 አለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት፤ አል-በሽርን በዘር ጭፍጨፋና የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የእስር ማዘዣ አውጥቶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ተያያዥ ርዕሶች