የብሬግዚት እቅድ በ432 የተቃውሞ ድምጽ ውድቅ ተደረገ

ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ Image copyright House of Commons
አጭር የምስል መግለጫ ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ

የጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ የብሬግዚት እቅድ በ230 የተቃውሞ ድምጽ ውድቅ ተደርጓል። ስልጣን ላይ ሳለ እንደዚህ አይነት ሰፊ የተቃውሞ ድምጽ የገጠመው መሪ የለም።

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የዋስ መብታቸው እንዲከበር ጠየቁ

ከቤተሰቦቿ አምልጣ ካናዳ የገባችው የሳዑዲዋ ወጣት፡ 'ምንም የሚጎልብኝ የለም'

የእንግሊዝ የሕዝብ እንደራሴዎች 432 ለ 202 በሆነ ድምጽ ነው እቅዱን ውድቅ ያደገሩት። የሌበር ፓርቲው መሪ ጀርሚ ኮርባይን፤ የመተማመኛ ድምጽ አለመኖሩን ማቅረባቸው ወደ አጠቃላይ ምርጫ ሊያመራም ይችላል።

የመተማመኛ ድምጽ ምርጫው ዛሬ የሚካሄድ ይሆናል።

ከሁለት ዓመት በላይ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ስለ እቅዱ ድርድር ያደረጉ ለነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ የተቃውሞ ድምጹ ትልቅ ሽንፈት ነው።

ከአፋር እስከ ዲሲ፤ በዚህ ሳምንት የሚጠበቁ ክስተቶች

እንግሊዝ፦ 'ከኢራን ጎን ነኝ'

እቅዱ እንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት ከወጣች በኋላ ለነጻ የንግድ ድርድር ወደ 21 ወር ገደማ የሚሰጥ ነበር።

ድምጽ መሰጠት የነበረበት በታህሳስ ወር ቢሆንም ጠቅላይ ሚንስትሯ የሕዝብ እንደራሴዎችን ድምጽ አገኛለሁ ብለው ተስፋ በማድረግ እንዲዘገይ አድርገዋል።

እንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት ግንቦት 29 መውጣቷ ባይቀርም፤ ጠቅላይ ሚንስትሯ ያቀረቡት እቅድ ውድቅ መደረጉ የአወጣጥ ሂደቱ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል።

ጠቅላይ ሚንስትሯ ያቀረቡትን የተለሳለሰ የብሬግዚት እቅድ የሚደግፉ፣ ተጨማሪ ሕዝበ ውሳኔ የሚሹ፣ ብሬግዚትን ከነጭራሹ የማይቀበሉ ወይም ከአውሮፓ ኅብረት ያለ ምንም ስምምነት መውጣት የሚፈልጉ የሕዝብ እንደራሴዎች የሚፈሉግትን ለማግኘት መጣጣራቸው ይገፉበታል።

ለጠቅላይ ሚንስትሯ አብላጫ ድምጽ በመስጠት ሀሳባቸውን የሚደግፉ የሕዝብ እንደራሴዎች ከጎናቸው የሉም። እየሄዱበት ያለውን አቅጣጫ የሚተቹም ተበራክተዋል።

ብሬግዚት በተለሳለሰ መንግድ ይከናወን ወይስ አይከናወን የሚለው የአቅጣጫ ጥያቄ የሁለቱ ተቃራኒ ወገኖች ንትርክ መነሻ ነው።

118 የሚሆኑ ወግ አጥባቂ የሕዝብ እንደራሴዎች ከተቃዋሚዎች ጋር ተመሳሳይ ድምጽ ሰጥተው የቴሬዛ ሜይን እቅድ ተቃውመዋል። በተቃራኒው ቴሬዛ ሜይ ሶሰት የሌበር የሕዝብ እንደራሴዎች ድጋፍ አግኝተዋል።

በምዕራብ ኦሮሚያ ምን ተከሰተ?

እንግሊዝ ሳዑዲን አስጠነቀቀች

መሰል የሕግ አርቃቂ አካላት ተቃውሞ ሲገጥም አንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሥራውን ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል። ቴሬዛ ሜይ ግን "ምክር ቤቱ የሚፈልገውን ተናግሯል መንግሥት ያደምጣቸዋል" ሲሉ ለሕዝብ እንደራሴዎች ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሯ በፓርቲዎች መካከል ስለ ብሬግዚት ውይይት በማድረግ ለወደፊት ስለሚወሰደው አቅጣጫ ለመወሰን ሀሳብ አቅርበዋል። ለዚህ ግን የዛሬውን የመተማመኛ ድምጽ ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።