ኳታር ለሶማሊያ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ለገሰች

የኳታር መንግሥት ለሶማሊያ 68 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ለገሰች።
የሶማሊያ መከላከያ ሚንስትር ሀሰን አሊ ሞሀመድ እና የሶማሊያ መከላከያ ሚንስትር ኃላፊ ዳሂር አዳን ኤልሚ፤ ሞቃዲሾ ውስጥ በተካሄደ የርክክብ ስነ ስርዐት መኪኖቹን ተቀብለዋል።
ጎብጆግ የተባለው የሶማሊያ ሚዲያ የኳታር አመራሮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የተለገሱት አል ሸባብን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ነው።
• ከሽብር ጥቃቱ ጋር በተገናኘ 9 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
• በሞቃዲሾ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር ከ270 በላይ ደርሷል
ጎብጆግ የሶማሊያ የመከላከያ ሚንስትር የኳታርን መንግሥትን ለልገሳው ማመስገናቸውንም ጨምሮ ዘግቧል።
የሶማሊያ መከላከያ ሠራዊት ከኳታር ወታደራዊ ኃላፊዎች ጋር በሞቃዲሾ በቅርቡ ተገናኝተው ነበር።
ኳታር የሶማሊያ መንግሥትን ከሚደግፉ ሀገሮች አንዷ ናት።