አብዲ ሞሃመድ ኡመር ላይ ክስ ተመሰረተ የሚልና ሌሎችም ዜናዎች

Image copyright BBC Somali

ኢትዮጵያ

• የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ አርባ ግለሰቦች ላይ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዛሬ ክስ መሰረተ።

ግለሰቦቹ ባለፈው ዓመት በሶማሌ ክልል ውስጥ በሚገኙ ነዋሪዎች መካከል ግጭት በመቀስቀስና በግጭቱ የሚሳተፍ ቡድን የማደራጀት ሕገ ወጥ ድርጊት ፈጽመዋል የሚል ክስ ነው የቀረበባቸው።

የቮልስ ዋገን መምጣት የመኪና ዋጋን ይቀንስ ይሆን?

ጉዳት የደረሰበት ታካሚ 440 ሺህ ዶላር ካሳ ተወሰነለት

ሱዳን

• በሱዳን ለሳምንታት በዘለቁት የፀረ-መንግሥት ተቃውሞ ሰልፎች ላይ የተያዙ እስረኞች በሙሉ እንዲለቀቁ መወሰኑን የሀገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ገልጿል።

በፈረንጆቹ ያለፈው ዓመት መጨረሻ ወር ላይ በጀመረው ተቃውሞ እስካሁን ከ1000 ሰዎች በላይ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እንዲፈቱ ያዘዙት ደግሞ የሱዳን መረጃና የደህንነት ኃላፊ ሳላህ ጎሽ ናቸው ተብሏል።

ጅቡቲ

• በጅቡቲ ጀልባ ተገልብጦ 28 የሚሆኑ ሰዎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ አስታወቀ።

አደጋው የተፈጠረው ትናንት ጎዶሪያ ከተባለ ቦታ የተነሳው ጀልባ ከአቅም በላይ ሰዎችን በመጫኑ እንደሆነም ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብቻ በእያንዳንዱ ቀን ስድስት ሰዎች የሜዲትራኒያንን ባህርን ሲያቋርጡ እንደሞቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

ህንድ

• የህንድ ፖሊስ አንዲት እናትን ከነአራት ልጆቿ የገደሉ ሰዎችን በማፈላለግ ላይ ነው።

ግለሰቦቹ እናትየዋን ከነልጆቿ የገደሏት ባዕድ አምልኮ አራማጆች ናቸው በሚል እንደሆነ ፖሊስ አስታውቋል።

ሰሜን ኮሪያ

• ሰሜን ኮሪያ ሙሉ በሙሉ የኒኩሌር መሳሪያዎች ማምረት እንደማታቆም የአሜሪካ የደህንነት ሪፖርት አስታወቀ።

በአሜሪካ የደህንነት ተቋም የተሰራው ሪፖርት አክሎም ኢራን ኒኩሌር መሳሪያ ማምረት ብታቆምም ቻይናና ሩሲያ የደህንነት ስጋት መሆናቸውን አመልክቷል።

ቬንዙዌላ

• የቬንዚዌላ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪው ሁዋን ጉአኢዶ ከሀገር እንዳይወጡና የባንክ ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ እገዳ ጣለባቸው።

ፖለቲከኛው ባለፈው ሳምንት ራሳቸውን የአገሪቱ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አድርገው መሾማቸው የሚታወስ ነው።

ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ የነበረው እስረኛ ጥቃት ደረሰበት

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በአል-ሻባብ ላይ ጥቃት ፈፀምኩ አለ

ሩሲያ

• አንድ ሩሲያዊ ህግ አውጪ በፈረንጆቹ 2010 ፈጽመውታል በተባለ ወንጀል ተጠርጥረው ፓርላማ ውስጥ እያሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ራኡፍ አራሹኮቭ የተባሉት ባለስልጣን በ2010 ከተፈጸመ የሁለት ሰዎች ግድያ እና ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ነው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው።

ታይላንድ

• በታይላንድ ሰማዮች ላይ ባጋጠመ የመርዛማ ጭስ ክምችት ምክንያት ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተዘገበ።

ተሽከርካሪዎች፣ የግንባታ ስራዎች፣ የሚቃጠሉ ማሳዎችና ትላልቅ ፋብሪካዎች ደግሞ ለመርዛማ ጭሱ ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች