የውሾችን ጩኸት ድንጋጌ በማውጣት መቆጣጠር ይቻላል?

ውሾች ሲጮኹ ባለቤቶቻቸው ይቀጣሉ ተብሏል Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ውሾች ሲጮኹ ባለቤቶቻቸው ይቀጣሉ ተብሏል

ጩኸት ውሾች እርስ በእርስ የሚግባቡበት ቀንቋ ነው። ፍርሀታቸውን፣ ጭንቀታቸውን የሚገልጹበትም መንገድ ነው።

ፈረንሳይ ውስጥ የሚገኝ ከተማ የውሾችን ጩኸት የሚያግድ ውሳኔ ማስተላለፉ "እንዴት ውሾች ከመግባባት ይታገዳሉ?" የሚል ጥያቄ አስከትሏል።

በሰሜናዊ ፈረንሳይ የሚገኘው ፌኩይሬስ ከተማ የ 1,400 ሰዎች መኖሪያ ነው። የከተማው ከንቲባ ዣን-ፒሬ ኤስቲኔ የድምጽ ብክለትን ለመከላከል ከመጠን ያለፈ የውሻ ጩኸት ማገዳቸውን አስታውቀዋል።

ወባን በማሽተት የሚለዩት ውሾች

ለህገወጥ አዳኞች ፈተና የሆኑት ውሾች

ውሻቸው ዘለግ ላለ ሰዓት ወይም ያለማቋረጥ የጮኸ የውሻ ባለቤቶች 77 ዶላር (2,156 ብር ገደማ) ይቀጣሉ።

ከንቲባው ውሳኔውን ያስተላለፉት ውሾች ቀን ከሌት በመጮሀቸው ከተማው እየረበሸ በመምጣቱ ነው ብለዋል። ሆኖም የእንስሳት መብት ተሟጋቾች ውሳኔውን ኮንነውታል።

ከንቲባው ስለ ውሳኔያቸው ለአንድ የፈረንሳይ ጋዜጣ ሲያስረዱ "አላማችን ውሾችን ማገድ አይደለም። ከተማችን ውሾችን አይጠላም። ነገር ግን ውሻ ያላቸው ነዋሪዎች ሥነ ሥርዐት የማስያዝ ግዴታ አለባቸው" ብለዋል።

ፍየሎችም «ከፍትፍቱ ፊቱ» ይሉ ይሆን?

በውሳኔው መሰረት ውሾች ከባለቤቶቻቸው ውጪ ለረዥም ሰአት በአንድ ቦታ መቆየት ተከልክለዋል። ይህም ውሾቹ መጮህ ቢጀምሩ የሚያስቆማቸው አይኖረም ከሚል ስጋት የመነጨ ነው።

በጣም የሚጮሁ ውሾች የከተማውን ነዋሪዎች ስለሚረብሹ ከሚኖሩበት ቤት መውጣትም አይችሉም። የውሻ ባለቤቶች ተደጋጋሚ ቅሬታ ከቀረበባቸው ለቅጣት ይዳረጋሉ።

ውሳኔው የተላለፈው የአንድ ሰፈር ነዋሪዎች ስለ አንዲት የውሻ ባለቤት በተደጋጋሚ ቅሬታ ካቀረቡ በኋላ ነበር። ሴትየዋ ብዙ ውሻዎች ያሏት ሲሆን፤ ውሾቹ "ለጸጥታ መደፍረስ ምክንያት ሆነዋል" ሲሉ ጎረቤቶቿ እሮሮ ያሰሙ ነበር።

'አሶሴሽን ፎር ዘ ዲፌንስ ኦፍ አኒማል ራይት' የተባለ የእንስሳት መብት ተሟጋች ተቋም መሪ ስቴፈን ላማርት ውሳኔው አልተዋጠለትም።

"የቤተክርስቲያን ደውል ድምጹ እንዳይሰማ ይከለከላል?" ሲል የውሾችን ጩኸት ማገድን ተቃውሟል። ለፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚልም ተናግሯል።

የውሾች የጩኸት መጠን ከውሻ ውሻ ቢለያይም፤ በድምጽ መለኪያ ሲሰላ የአንድ ውሻ ጩኸት በአማካይ ከአንድ ፋብሪካ ማሽን ድምጽ በበለጠ የጎላ ነው።

ቻርሊ የተባለ አውስትራሊያዊ ውሻ ከዓለም ውሾች አብልጦ በመጮህ አንደኝነቱን ይዟል።

ተያያዥ ርዕሶች