እድሜ ጠገቡ የፍቅር ካርድ ነገ ለጨረታ ይቀርባል

እድሜ ጠገቡ የፍቅር መልዕክት Image copyright Hansons
አጭር የምስል መግለጫ እድሜ ጠገቡ የፍቅር መልዕክት

የዓለም እድሜ ጠገብ የፍቅር መልዕክት ነው የተባለው የፍቅረኞች ቀን ካርድ ነገ ለጨረታ ይቀርባል። ነገ በሚከበረው የፍቅረኞች ቀን ለጨረታ የሚቀርበው ካርድ እስከ 400 ፓውንድ(14600 ብር ገደማ) እንደሚያወጣ ተገምቷል።

'ሀንሰንስ አውክሽነርስ' የተባለ የጨረታ ተቋም ኃላፊ ቻርለስ ሀንሰን፤ የቪክቶሪያን እና የግሪጎሪያን ካርድ ሲሰበስቡ ካርዱን እንዳገኙት ተናግረዋል።

የፍቀረኞችን ቀን ያከብራሉ? ለምን?

እንደ እውሮፓዊያኑ በ1970ቹ እንደነበረ የተገመተውን ካርድ "በጣም ልዩ" ሲሉ ገልጸውታል።

Image copyright Hansons
አጭር የምስል መግለጫ ካርዱ ላይ የሚነበበው የእጅ ጽሁፍ

ካርዱ ላይ "አንቺ ጣፋጭ እርግብ ደህና ሁኚ፤ የምወደው አንቺን ብቻ ነው፤ አንቺ የኔ ካልሆንሽ መቼም ምቾት አይሰማኝም" የሚል የእጅ ጽሑፍ ይነበባል።

ሀንሰን እንደተናገሩት ከወረቀት የተሰራው የፍቅር ካርድ ቢቀደድም ጥንታዊ የካርድ አሰራርን ያሳይል። ካርዱ ጉዳት የደረሰበት ለተቀባይ ለመላክ ሲታጠፍ መሆኑንም አስረድተዋል።

'ለምን ብዙ ወንዶች በመጀመሪያው የፍቅር ቀጠሮ ሒሳብ መክፈል ይኖርባቸዋል'

"ካርዱ ላይ የሰፈረው መልዕክት ከልብ የመነጨ ነው። ፍቅሩ የተገለጸበት መንገድ ልብ ይነካል" ብለዋል።

Image copyright Hansons
አጭር የምስል መግለጫ ካርዱ ካይ የሚገኘው ምስል

ካርዱ በእንግሊዝ ውስጥ ከ1949 እስከ 1990 ከተሰባሰቡ ቅርሶች አንዱ ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ ካርድ የታተመው እንደ አውሮፓውያኑ በ1979 አንደሆነ ይታመናል። የመጀመሪያው የእንግሊዘኛ የፍቅረኞች ቀን ካርድ የተጻፈው በ1477 ነው።

ትዳር ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል

በፍቅረኞች ቀን ፍቅርን የሚገልጹ ስጦታዎችና፣ ፖስት ካርዶች መለዋወጥ የተለመደ ነው።