"ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀላ አንገት በቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ማየቴ አልረበሸኝም"

እንግሊዝን ስትለቅ 15 ዓመቷ ነበር Image copyright Met Police
አጭር የምስል መግለጫ እንግሊዝን ስትለቅ 15 ዓመቷ ነበር

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 ምስራቅ ለንደንን ለቃ ኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) የተቀላቀለችው ሻሚማ ቤጉም ወደ እንግሊዝ መመለስ እንደምትፈልግ አስታውቃለች።

የ19 ዓመቷ ታዳጊ እንግሊዝን ለቀው ከወጡ ሦስት ልጆች አንዷ ስትሆን፤ ውሳኔዋ እንደማይጸጽታት ተናግራለች።

በእንግሊዝ ሳለች የትምህርት ቤት ጓደኛዋ የነበረችውና አብራት ወደ ሶሪያ ያቀናችው ጓደኛዋ፤ በቦምብ ፍንዳታ እንደሞተች ተናገራለች። የሶስተኛዋ ልጅ እጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ግን አልታወቀም።

ሶሪያ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ያለችው ሻሚማ፤ የዘጠኝ ወር ነፍሰ ጡር መሆኗን ተናግራ ልጇን ለመውለድ ወደቤቷ መመለስ እንደምትፈልግ ተናግራለች። ከዚህ በፊት ሁለቴ ብትወልድም ሁለቱም ሞተውባታል።

የ 'ቤተናል ግሪን' አካዳሚ ተማሪዎች የነበሩት ሻሚማና አሚራ ቤዝ እንግሊዝን በ 2015 ሲለቁ 15 አመታቸው የነበረ ሲሆን፤ ካዲዛ ሱልጣን ደግሞ 16 ዓመቷ ነበር።

አልሸባብ አይኤስ ላይ ጦርነት አወጀ

ፖሊስ የላስ ቬጋሱ ታጣቂ ጥቃቱን ለመፈፀም ምን እንዳነሳሳው እያጣራ ነው

ከጋትዊክ አየር ማረፊያ ወደ ቱርክ የሄዱት "ለአጭር ቀናት" በማለት ለቤተሰቦቻቸው ተናግረው ቢሆንም በኋላ ግን የሶሪያን ድንበር አልፈው አይኤስን ተቀላቀሉ።

ራቃ ሲደርሱ ሻሚማ ሙሽራ ልትሆን ከተዘጋጀች ልጅ ጋር በአንድ ቤት እንደተቀመጡ ለ 'ዘ ታይምስ' መፅሔት ተናግራለች።

"እንግሊዘኛ ተናጋሪ የሆነና እድሜው ከ20 እስከ 25 የሚሆን ሰው ለማግባት ጠየቅሁ" ትላለች።

ከአስር ቀን በኋላ ወደ እስልምና እምነቱን የቀየረ የ27 ዓመት ሆላንዳዊ ወጣት አገባች። ከዛ ጊዜ ጀምራ ከሱ ጋር የቆየች ሲሆን፤ ጥንዶቹ የቡድኑ የመጨረሻ ግዛት ከነበረው ምስራቃዊ ሶሪያ ባጉዝ ከሁለት ሳምንት በኋላ አምልጠው ሄዱ።

የትዳር አጋሯ ለሶሪያ ተዋጊዎች እጁን የሰጠ ሲሆን፤ እሷ ግን በሰሜናዊ ሶሪያ ከ39 ሺህ ስደተኞች ጋር በስደተኞች መጠለያ ውስጥ ትገኛለች።

በአንድ ቤተሰብ አባላት የተቀነባበረው የሽብር ጥቃት

ትራምፕ ቱርክን አስጠነቀቁ

በ 'ዘ ታይምስ' ጋዜጠኛ አንቶና ሎይድ የአይኤስ ተዋጊዎች ጠንካራ ግዛታቸው የነበረው ራቃ እንደጠበቀችው አግኝታው እንደሆነ ተጠይቃ "አዎ፤ በየሰዓቱ ቦንብ ፍንዳታ ነበር። ከዚያ ውጪ ግን መደበኛ ህይወት ነበር" ብላለች።

"ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀላ አንገት በቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ማየቴ አልረበሸኝም" ብላለች። ከእንግሊዝ መውጣቷ እንደማይጸጽታትም ተናግራለች።

"የዛሬ አራት አመት ከትምህርት ቤት ጠፍቼ የሄድኩት የ15 ዓመት ትንሽ ተማሪ አይደለሁም" ስትል ለጋዜጠኛው ተናግራለች።

Image copyright Met Police
አጭር የምስል መግለጫ ከግራ ወደ ቀኝ ካዲዛ ሱልጣን፣ አሚራ አባስ እና ሻሚማ ቤገም

የሌላዋ ሴት የካዲዝ ሱልጣን ቤተሰብ ጠበቃ በ2016 በሩሲያ የአየር ጥቃት ሞታለች ብለው እንዳሰቡ ይናገራል።

ሻሚማም ለ' ዘ ታይምስ' እንደተናገረችው ጓደኛዋ በአየር ድብደባው "ድብቅ ነገር ይካሄድበት በነበረ ቤት ውስጥ" እንደተገደለች ተናግራለች።

አክላም "እንዲህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም። መጀመሪያ ላይ ውሸት ነው ብዬ ነበር። ከተገደልንም አብረን እንገደላለን ብዬ ነበር የማስበው" ብላለች።

ሻሚማ ሁለት ልጆች ማጣቷ ድንጋጤ ፈጥሮባት ነበር። የመጀመሪያ ልጇ ሴት የነበረች ሲሆን፤ በአንድ አመት ከዘጠኝ ወሯ ባጉዝ በሚባል ስፍራ ነው የተቀበረችው።

ሁለተኛ ልጇ ከመጀመሪያ ልጇ ቀድማ የሞተች ሲሆን፤ ከሶስት ወር በፊት የስምንት ወር ልጅ እያለች በምግብ እጥረት ነው የሞተችው። ለዛም ነው አሁን በሆዷ ላለው ልጅ የበለጠ የምትንሰፈሰፈው።

ሱዳን ውስጥ የዳቦና የነዳጅ ዋጋ ንሮብናል ያሉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ

ይህ ሁኔታዋ ባጉዝን ለቆ ለመሄድ አንድ ምክንያት እንደሆናት ትናገራለች።

"ደካማ ነኝ። ስቃይና እንግልት በበዛበት የጦር ሜዳ መቆየት አልችልም" በማለት "በተጨማሪም እዚህ ከቆየሁ በሆዴ ያለውን ልጅ እንደሌሎች ልጆቼ አጣዋለሁ ስል እሰጋለሁ" ብላለች።

"ለዚያም ነው ወደ እንግሊዝ መመለስ የምፈልገው። ቢያንስ ቢያንስ የልጄን ጤንነት እንደሚንከባከቡት አውቃለሁ" ብላለች።

አይኤስ በኢራቅና በሶሪያ ይቆጣጠራቸው የነበሩትን ጠንካራ ግዛቶቹን ማጣቱ ይታወሳል። ነገር ግን አሁንም በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ ውጊያ የቀጠለ ሲሆን፤ የኩርድ አማፅያን በርካታ የውጭ ሀገር ተዋጊዎችን መያዛቸውን እየተናገሩ ነው።