አረና ብሄራዊ የአንድነት መንግሥት እንዲቋቋም ጥሪ አቀረበ የሚሉና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

ኢትዮጵያ፦

አረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን መቋቋምን እንደሚቃወም አስታወቀ።

እስከ መጭው ምርጫ ድረስም ብሄራዊ የአንድነት መንግስት እንዲቋቋም ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።

ህንድ ውቅያኖስን ለማቋረጥ ሲሞክሩ የሞቱ ስምንት ኢትዮጵያዊያን ቀብር ዛሬ በታንዛኒያ ታንጋ ተፈፅሟል።

ኢትዮጵያዊያኑ የሞቱን ጥቅምት ወር ላይ ሲሆን አስከሬናቸው የቆየው በታንዛኒያው ታንጋ ሆስፒታል ነበር።

በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው?

ኬንያ፦

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አምስት የፖሊስ አዛዦችን በስድስት ወር ህፃን ሞት ጥፋተኛ ብሏል።

ፖሊሶቹ ከሁለት ዓመታት በፊት በኬንያ የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ ተቃውሞ በተቀሰቀሰበት ወቅት ነው ህፃኗን ደብድበው ገድለዋል የተባለው።

በሌላ ክስ ደግሞ ፍርድ ቤቱ እስረኛን በመግደል ሌላ የፖሊስ አዛዥ ላይ የሞት ቅጣት ወስኗል።

ጤፏን ለማስመለስ እየተውተረተረች ያለችው ኢትዮጵያ

ሱዳን፦

ሱዳናዊው ኢሰብአዊ ነው ያለውን የአውስትራሊያ ስደተኞችን አያያዝ በማጋለጡ ከፍተኛ የተባለውን የሰብአዊ መብት ሽልማት አገኘ።

የ26 ዓመቱ አብዱል አዚዝ ሙሃማት ከዳርፉር ሸሽቶ በአውስትራሊያዋ ማነስ ደሴት እስር ቤት ለስድስት አመታት የቆየ ሲሆን በነዚህ ጊዜአት ታሪኩን በፖድካስት ለሚነግርለት ጋዜጠኛ በሺህዎች የሚቆጠሩ የዋትስ አፕ መልእክቶችን ልኳል።

ዚምባብዌ፦

ከዙምባብዌ የካዶማ ከተማ ሁለት የማእድን ሳይቶች በርካታ ወርቅ አውጪዎች በጎርፍ ተወስደዋል እየተባለ ነው።

ከሃይለኛው ዝናብ በኋላ የነፍስ አድን ሰራተኞች ቢሰማሩም እስከ አሁን በህይወት የተገኘ እንደሌለ ተገልጿል።

ኢራን፦

የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሃሳን ሮሃኒ ግዛቶቻችሁን የሽብርተኛ መጫወቻ አታድርጉ ሲሉ ጎረቤቶቻቸውን አስጠንቅቀዋል።

ሮሃኒ ይህን ያሉት በአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ 38 የኢራን አብዮት ጠባቂዎች መገደላቸውን ተከትሎ ነው።

ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ

አሜሪካ፦

በአሜሪካ የሚደገፈው የሶሪያ ተዋጊዎች ቡድን በአይ ኤስ ይዞታ ስር ያሉ የመጨረሻዎቹን ሁለት ቦታዎች ለማስለቀቅ መቃረቡን የአሜሪካ ወታደራዊ ሃላፊዎች ገለፁ