ከተለያየ አባት የተወለዱት መንትዮች

ሳይመንና ግራይም በርኒ- ኤድዋርድስ ልጆቻቸው አሌክሳንድራና ካልደርን አቅፈው
አጭር የምስል መግለጫ ሳይመንና ግራይም በርኒ- ኤድዋርድስ ልጆቻቸው አሌክሳንድራና ካልደርን አቅፈው

አሌክሳንድራና ካልደር ይባላሉ። መንትያ እህትና ወንድም ሲሆኑ፣ ከተወለዱ 19 ወራት ተቆጥሯል።

መንትዮቹን ለየት የሚያደርጋቸው ከአንድ እናት እና ከሁለት አባት መወለዳቸው ነው።

አሌክሳንድራ የሳይመን ልጅ ናት። ወንድሟ ካልደር ደግሞ የግራይም።

ለመሆኑ መንትዮች እንዴት ከተለያየ አባት ይወለዳሉ?

ልብ የረሳው አውሮፕላን

በሰው ክፋይ ሕይወት መዝራት - የኩላሊት ንቅለ ተከላ

ሦስት ሀገሮች፣ አራት የቤተሰብ አባላት፣ ሁለት ልጆች

ሳይመንና ግራይም በርኒ- ኤድዋርድስ አይቪኤፍ ወይም ቪትሮ ፈርቲላይዜሽን በመጠቀም ልጅ ለመውለድ ከሚወስኑ ጥቂት እንግሊዛውያን ጥንዶች መካከል ናቸው።

አይቪኤፍ በቤተ ሙከራ ውስጥ እንቁላል ከወንድ ዘር ፍሬ ጋር ተዋህዶ ጽንስ የሚፈጠርበት መንገድ ነው።

ሳይመንና ግራይም ልጆች ያገኙበት ሂደት ቀላል አልነበረም።

በሕይወት ከሌለች እናት የተወለደችው ሕፃን

በመጀመሪያ እንቁላል ማግኘት ነበረባቸው። ሀሳባቸው ከሁለት የኪራይ እናቶች (በእንግሊዘኛ ሰረጌት ማዘር የሚባለው) ሁለት ልጆች ለመውለድ ነበር።

ሆኖም በሂደቱ የሚያግዛቸው ተቋም ከአንድ እንቁላል ለጋሽ በአንድ የኪራይ እናት ሁለት ልጆች በአንድ ጌዜ ማግኘት እንደሚቻል አሳወቃቸው።

ቀጣዩ የሂደቱ ክፍል እንቁላል ማግኘት ነበር። ሳይመን "ማንነቷን ከማናውቅ አሜሪካዊት ለጋሽ እንቁላል አገኘን" ይላል።

ስለዚህም ሁለቱም በአንድ ጊዜ የዘር ፍሬያቸውን ለአንዲት የኪራይ እናት ሰጡ።

አጭር የምስል መግለጫ ሳይመንና ግራይም ልጆቹን ከወለደችው ሜግ ስቶን ጋር

የለጋሿ እንቁላሎቹ ለሁለት ከተከፈሉ በኋላ ግማሹ ከሳይመን ዘር ሌላው ግማሽ ደግሞ በግራይም ዘር ጋር ተዋህዶ ጽንስ እንዲፈጠር ተደረገ።

ከዛም ካናዳ ውስጥ ልጆቹን አርግዛ የምትወልድ የኪራይ እናት አገኙ።

ካናዳዊት የቅጥር እናት

ሜግ ስቶን ሁለቱን ልጆች የወለደችው ካናዳዊት የኪራይ እናት ናት።

"ካናዳን የመረጥነው የሕግ ማዕቀፋቸውን ስለምንወደው ነው። ነገሩ የሚከናወነው እንደ ንግድ ሳይሆን ከልብ በመነጨ የመተባበር ስሜት ነው" ሲል ሳይመን ያስረዳል።

ሁለቱ አባቶች ልጆች ማግኘት እንደሚችሉ የምስራች የሰሙት እንግሊዝ ሳሉ ነበር። ግራይም ቅጽበቱን ሲገልጽ "በጣም ስሜታዊ ሆነን ነበር። እጅግ በጣም ተደስተን ነበር" ይላል።

ሳይመንና ግራይም የተረገዙት ልጆቻቸውን እድገት የሚከታተሉት ከእንግሊዝ ሆነው ነበር። ልጆቹ ሊወለዱ ስድስት ሳምንት ሲቀራቸው ደግሞ ወደ ካናዳ አቀኑ።

አባቶቹ ከኪራይ እናቷ ሜግ ስቶን ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ።

ሳይመንና ግራይም አሁን በተወለዱት ልጆች ደስተኛ ቢሆኑም፤ ለወደፊት ተጨማሪ ልጅ ሊወልዱ የሚችሉበት እድል እንዳለ ሳይመን ጠቁሟል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ