በማይታዩ ፕሬዚዳንት የምትመራው አልጀሪያ

አብደላዚዝ ቡተፍሊካ Image copyright AFP

የአልጀሪያው ፕሬዝዳንት አብዱላዚዝ ቡተፍሊካ የ82 አመት አዛውንት ናቸው።

እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ2014 በሀገሪቱ በተካሄደው ምርጫ አሸንፈው በ1999 የተረከቡትን ስልጣን ሲያስቀጥሉ በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ብለው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከዚያን ቀን ጀምሮ ግን የውሃ ሽታ ሆነዋል። ሀገሪቱም በማይታይ ፕሬዚዳንት መመራት ከጀመረች እነሆ ስድስት አመት ሆናት።

በ82 ዓመት አዛውንት የምትመራው አልጄሪያ ፈተና ገጥሟታል

ለስድስት አመታት አልጀሪያውያን ፕሬዝዳንታቸውን አይተዋቸው አያውቅም። አሁን ላይ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ ፕሬዝዳንቱ መናገር አይችሉም ፤ እራሳቸውንም መርዳት ስለማይችሉ በጋሪ (wheelchair) እየተገፉ ነው የሚንቀሳቀሱት።

ይህም ምስል የተገኘው ከሶስት አመት በፊት የሀገሪቱን ፓርላማ ሲከፍቱ በተደረገ አጭር ቀረጻ ነው።

የእኩልነት አለም ብለው የሚገልጿት የአውራምባውያኑ አምባ

በዚህ ሶስት አመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ የበለጠ ተዳክመው እንደሚሆን ይጠበቃል። ነገሮች በአወዛጋቢነታቸው ቢቀጥሉም በእንደዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነውም በሚቀጥለው ሚያዝያ አልጀሪያ ለምታካሂደው ምርጫ ሊወዳደሩ ይችላሉ መባሉ ግርምትን አጭሯል።

ይህን ተከተሎም የአልጀሪያ ተማሪዎች ፥ መምህራንና ጋዜጠኞች ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው።

ይህ በመሆኑም ካሁን በፊት በጎረቤቶቿ ሊቢያ እና ቱኒዚያ የነበረው የርስበርስ ጦርነት በአልጀሪያም እንዳይደገም ተሰግቷል።

"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው"

በአልጀሪያ በ2002 በተጠናቀቀው የርስ በርስ ግጭት 150000 ዜጎች ህይዎታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።

አልጀሪያ በ1962 ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ካገኘችበት ጊዜ ጀምሮ አሁን ስልጣኑን በያዘው ፓርቲ ብቻ ነው እየተመራች የምትገኘው።

ተያያዥ ርዕሶች